Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

-አንድ ጋዜጠኛና አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባልን ጨምሮ በርካቶች መታሰራቸው ተጠቁሟል ‹‹አብዛኛዎቹ ተለቀው ለግጭቱ ምክንያት የሆኑት ብቻ ታስረዋል›› ፖሊሶች ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ለጁምዓ (እለተ ዓርብ) ፀሎት መርካቶ በሚገኘው ታላቁ የአንዋር መስጊድ ተገኝተው የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሰሙት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት በመፈጠሩ፣ የተጎዱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ የተለያዩ ግለሰቦችና…
የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆንና የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን መርተዋል በሚል ተጠርጥረው ብቻቸውን በተከሰሱበት ክስ ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ከሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የሙያ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ፡፡  በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ ብቻ በክስ መዝገብ ቁጥር 141354 በሁለተኛ ክስነት የቀረበባቸውን…
‹‹የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ ስለተጠቀሰ ብቻ ሽብር ተፈጽሟል ማለት አይቻልም›› የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ የቀረበባቸው ክስ በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን ዋስትና የማግኘት መብት የሚጋፋ በመሆኑ፣ የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤትን ጠየቁ፡፡  የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ዋስትና ማግኘት መብት መሆኑን ደንግጎ ሳለ፣ በጠቅላላው…
የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዳኝነት ችሎት  ሲመለከታቸው በቆዩ ሦስት ጉዳዮች ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ውሳኔ ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባለሥልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በንግድ ውድድርና በሸማቾች መብት ጥሰቶችን የመከታተልና ዕርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለበት፡፡  በዚህ መሠረት ለመጀመርያ ጊዜ ከሸማቾችና ከንግድ ውድድር ጋር የተያያዙ ናቸው ባላቸውና እስካሁን ሲታዩ ከነበሩ ጉዳዮች ውስጥ በሦስቱ…
-የታሳሪዎቹ ጠበቃ የሥነ ሥርዓት ሕጉ ተጥሷል ይላሉ -ፍርድ ቤቱ በ48 ሰዓት ውስጥ መቅረባቸውን አረጋግጫለሁ ብሎ ብይን ሰጥቷል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል፣ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን የአንድነት፣ የሰማያዊና አረና (ትግራይ) ፓርቲዎች አመራሮች በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት አቅርቦ የ28 ቀናት…
ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ዋና ቃዲ (ምክትል ፕሬዚዳንት) ሼክ አማን ሽፋው ዓለሙ ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ…
-ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቤያለሁ ብሏል ‹‹ግብረ ኃይሉ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ስለማቅረቡ ማስረጃ አላቀረበም›› የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ የተጠረጠሩበት ወንጀል ግልጽ ሳይደረግላቸው ከመታሰራቸው በተጨማሪ በሕገ መንግሥቱ ‹‹ዜጎች ተጠርጥረው በታሰሩ 48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው የሚገልጸውን ድንጋጌ ተላልፏል›› በሚል በአንድነት ፓርቲ ክስ የተመሠረተበት፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር…
አንድነት ፓርቲ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት በ48 ሰዓታት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በእስር መቆየታቸው ሕገወጥ ነው ሲል ላቀረበው ክስ በአራዳ የሚገኘው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው ማስረጃ ማቅረቡን በመግለጽ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ብይን ሰጠ፡፡ የተያዙበት መንገድ ሕገወጥ ነው…
በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጦማሪያን፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ እንዲሁም ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ላይ ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የሽብርተኝነት ወንጀል በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተሳታፊ በመሆን ለአመፅ ተግባር…
የፌዴራል የስነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮምሽን ያልተገባ ግዥ ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ የፅሕፈት ቤቱ የግዥ ስራ ሂደት ኃላፊ እና የእቃ አቅራቢ ደርጅት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሆኑትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡   ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር…
‹‹ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያስረው በምርጫ 2007 ያለተቀናቃኝ ለማለፍ ነው›› ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የታሰሩት ከምርጫ ጋር በተገናኘ ሳይሆን በሽብር ስለተጠረጠሩ ነው›› መንግሥትበምን እንደተጠረጠሩ ግልጽ ሳይደረግላቸው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሐዊ ፓርቲ (አንድነት)   ሥራ አስፈጻሚና ምክር ቤት አባላትን በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ…
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለባለጉዳዮችና ለመላው ሕብረተሰብ በቀላሉ መረጃ ለመስጠት ያስገነባው 992 የነፃ የጥሪ ማዕከል በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡ ከጥር/2006 ዓ.ም. ጀምሮ በሙከራ ላይ ቆይቶ ሰኔ 13/2006 ዓ.ም. በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ክቡር አቶ ተገኔ ጌታነህ በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረው የነፃ የጥሪ ማዕከል የፍ/ቤቱን ተገልጋዮች ጨምሮ ለዜጐች ወቅታዊና ፈጣን መረጃ በመስጠት…
-እነ አቶ መላኩ ፈንታ ለብይን ተቀጠሩ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ በመዝገብ ቁጥር 141356  ‹‹ማሻሻል የለብኝም›› ብሎ ለይግባኝ ያቀረበውንና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገበትን ክስ አሻሽሎ፣ ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ብይን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቀረበ፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ…
ኖርዌይ ዜግነት ያላቸው የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ (ቅጽል ስም መኖሪያ ካዋናሞ)፣ ሦስት የደቡብ ሱዳን ዜጐችና አራት ኢትዮጵያውያን የተጠረጠሩበትን የሽብርተኝነት ክስ በመቃወም ለፍርድ ቤት ሰኔ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. አቤቱታ አቀረቡ፡፡   የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ፣ በተለይ አቶ…