Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

-የፋክትና የአዲስ ጉዳይ መጽሔቶች ተከሳሾች አልቀረቡም -የሎሚ መጽሔት ሥራ አስኪያጅ የ50 ሺሕ ብር ዋስ ተጠየቁ ፍትሕ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ክስ መሥርቼባቸዋለሁ ያላቸው የፋክት፣ የአዲስ ጉዳይ፣ የዕንቁ፣ የሎሚ፣ የጃኖ መጽሔቶችና የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ አሳታሚ ድርጅቶችና የድርጅቶቹ ሥራ አስኪያጆች ጉዳይ፣ ከነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በፍርድ ቤት መታየት…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የአዲስ ጉዳይ መፅሄት ዋና ሰራ አስኪያጅን ክስ ተመለከተ። የፍትህ ሚኒስቴር በአምስት መፅሄቶች እና በአንድ ጋዜጣ ላይ ከአንድ ሳምንት በፊት ክስ መመስረቱ እና በትናንትናው እለትም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት የፋክት መጽሄት ዋና ስራ አስኪያጅ የተመሰረተባቸውን ክስ መመልከቱ ይታወሳል። ፍርድ ቤቱ…
ዋስትና የተፈቀደላቸው ሦስት ተጠርጣሪዎች በይግባኝ ውድቅ ተደረገባቸው ‹‹ስለጋዜጠኛዋና የፖለቲካ ፓርቲ አባሏ ለፍርድ ቤቱ በሚስጥር የምናስረዳው አለን›› መርማሪ ፖሊስ በአንዋር መስጊድ ነበረ በተባለ ብጥብጥና ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩትና በእስር ላይ የሚገኙት የፖሊስ አባላት፣ ‹‹የሠራነው ወንጀልም ሆነ የፈጸምነው ረብሻ የለም፣ የታሰርነው ከመስጊድ ውስጥ ስንወጣ የአድማ በታኝ ፖሊስ አባል መሆናችን የሚገልጽ መታወቂያ በማሳየታችንና…
በሌለችበት የተከሰሰችው ጦማሪ በጋዜጣ እንድትጠራ ድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጠ በሽብርተኝነት ወንጀል በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው ከታሰሩ 100ኛ ቀናቸውን ባስቆጠሩበት ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የነበሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን፣ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ መቃወሚያ አቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በዕለቱ ተቀጥረው የነበረው በሌለችበት…
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ ለመናድ በማሴር የተጠረጠሩ የህትመት ውጤት አሳታሚዎችና ድርጅቶች ተከሰሱ። የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፥ በየጊዜው ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሀይል እንዲፈረስ  እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን…
-እስራኤላዊው የትድሃር ኩባንያ ባለቤት ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኦዲት የቡድን መሪና ሁለት የታክስ ኦዲተሮች፣ መንግሥትን ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲያጣ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ሐምሌ 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ታሰሩ፡፡ ከባለሥልጣኑ ኦዲተሮች በተጨማሪ ትድሃር ኤክስካቬሽን ኤንድ ኧርዝ ሙቪንግ የግል ኩባንያ የተባለው…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን የበራራ ቁጥሩ ET-702 ቦይንግ 767 አውሮፕላንን የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. በመጥለፍ ወንጀል በሌለበት ክስ የተመሠረተበት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ላይ፣ ዓቃቤ ሕግ ሐምሌ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ምስክሮቹን አሰማ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በረዳት አብራሪው ላይ የመሠረተውን የአውሮፕላን መጥለፍ ወንጀልና የአውሮፕላንን ደኅንነት አደጋ ላይ…
ከ500 ካሬ ሜትር ቦታ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረውና ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለአሥር ወራት በማረሚያ ቤት ሆነው ሲከራከሩ ከከረሙ በኋላ፣ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በነፃ ተሰናብተው በነበሩት እነ አቶ ቃሲም ፊጤ ላይ ይግባኝ ተባለ፡፡  ይግባኙን የጠየቀው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ…
አገር አቀፍ ነፃ የሕግ ድጋፈ ሰጪዎች ቅንጅትን ለማቋቋም ሐምሌ 24 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም.በፍሬንድሺኘ ኢንተርናሽናል ሆቴል የተዘጋጀው የአውደ ምክክር መርሃ ግብር የቅንጅቱን ማቋቋሚያ ሰነድ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡ የምክክር መድረኩን በመክፈት ንግግር ያደረጉት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ም/ኘሬዚዳንት አቶ መድሕን ኪሮስ እንዳሉት ፍትህ የማግኘት መብት የአገሪቱ የበላይ ሕግ በሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትና አገሪቱ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፉ ሰብአዊ…
የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በተናጥል በቀረቡባቸው ክሶች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን የመስማት ሂደት በመጪው ሳምንት በጊዜ መጣበብ ምክንያት ሊካሄድ የማይችል ከሆነ ለመጪው ዓመት ይተላለፋል በማለት ፍ/ቤቱ መደበኛ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት፣ ከትናንት በስቲያ ሀሙስ በጠዋት ክፍለ ጊዜው የአቃቤ ህግን አንድ ምስክር ካስደመጠ በኋላ፣…
ያለምንም የትምህርት ዝግጅትና ተገቢ እውቅና ራሱን ዶክተር ኢንጂነር ብሎ ሲጠራ የነበረው ሳሙኤል ዘሚካኤል በኬኒያ በቁጥጥር ሰር ዋለ። ሳሙኤል ዘሚካኤል በፋና ብሮድካስት ዶክተር ኢንጂነርነቱ የሀሰት መሆኑ መጋለጡና በተለያዩ ተቋማትና  ግለሰቦች ላይ የማታለል ድርጊት መፈፀሙን ይፋ መደረጉን ተከትሎ ከሀገር መውጣቱ ሲነገር ቆይቷል። የአዲስ አበባ  ፖሊስ ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀውና ፋናም እንደዘገበው፥ ከኬኒያ ፖሊስ…
ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የውስጥ ገቢ የመጠቀምና የማስተዳደር ሥርዓት ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ የሚያስችል መመርያ ማዘጋጀቱን፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡   በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ ተፈርሞ ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከው ደብዳቤና በአባሪነት የተያያዘው መመርያ…
-ጂኦቴል የሞባይል መገጣጠሚያ ሁለት ሞዴሎችን እንዳያመርት ታገደ -ሊፋን ሞተር ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ ቴክኖ ሞባይል መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሁለት የሞባይል ምርቶቹን አስመስሎ ሠርቶብኛል ያለውን ጂኦቴል የሞባይል ፋብሪካን ያልተገባ የንግድ ውድድር አድርጓል በሚል በመሠረተበት ክስ፣ ተመሳስለው የተሠሩ ናቸው የተባሉት ሁለቱ የጂኦቴል ሞባይል ቀፎዎች ምርት እንዲቆም ውሳኔ ተላለፈ፡፡  ይህንን ውሳኔ የወሰነው የሁለቱን…
በሥራ ላይ የሚገኘውን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች አዋጅን ለማሻሻል የተረቀቀውን አዋጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ዓርብ በማፅደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ፡፡ ረቂቅ አዋጁ በ1996 ዓ.ም. ፀድቆ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘውን አዋጅ የተወሰኑ ድንጋጌዎች የሚያሻሽልና ተጨማሪ ድንጋጌዎችንም ያካተተ መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተለይ ወሳኝ የተባሉ ሁለት ድንጋጌዎች በረቂቁ…