Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

አስፈላጊውን የስደተኞች ሥነ ሥርዓት ሳያሟሉ ወደ አገሬ ገብተዋል በማለት ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ዛምቢያ በ26 ኢትዮጵያውያን ላይ የአንድ ዓመት እስራት፣ ከባድ የጉልበት ሥራና 4,500 የዛምቢያ የገንዘብ (ኩዋቻ) ቅጣት አስተላለፈች፡፡ ታይምስ ኦፍ ዛምቢያ በድረ ገጹ የዛምቢያ ስደተኞች ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናማቲ ሺንካን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በ26 ኢትዮጵያውያን ላይ ውሳኔው የተላለፈው የስደተኞች ጉዳይ…
-ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ቢፈጸም ተገቢ ዕርምጃ እወስዳለሁ አለ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው ጋዜጠኞችና ጦማሪያን መካከል፣ ሴት ጦማሪያን ማኅሌት ፋንታሁንና ኤዶም ካሣዬ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እየደረሰባቸው ያለውን በደል በሚመለከት ለፍርድ ቤት ያቀረቡትን አቤቱታ፣ ማረሚያ ቤቱ ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አስተባበለ፡፡ የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት አስተዳደርን ወክለው ፍርድ ቤት የቀረቡትና…
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሃይማኖት አባት የነበሩትን፣ ሼክ ኑሩ ይማምን በመግደል ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ 14 ተጠርጣሪዎች፣ የተመሠረተባቸውን ክስ እንዲከላከሉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን ሰጠ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን የሰው መግደል ወንጀል ክስ ተጠርጣሪዎቹ ክደው በመከራከራቸው፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል…
ተጠርጣሪው በሌላ ወንጀል 12 ዓመታት ተፈርዶባቸው ሲፈለጉ እንደነበር ተገልጿል በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ውስጥ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ዳንኤል ዋለልኝ የተባሉ የሕግ ባለሙያን በጥይት ገድለው መሰወራቸው የተገለጸው ባለሀብት፣ ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታወቀ፡፡ ባለሀብቱ አቶ…
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጡትን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በሽብር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ 13 ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው። ተከሳሾቹ እስማኤል ኑር ሁሴን፣ ፈትያ መሃመድ፣ ኑርዬ ቃሲም፣ ያሲን ፈያሞ፣ መሃመድ አሚን፣ መሃመድ ሰይድ፣ የሱፍ ከድር፣ ጣሂር መሃመድ፣ መሃመድ ሰይድ፣ ሰይድ ኢብራሂም፣ አብደላ መሃመድ፣ አብዲ መሃመድ እና ኢብራሂም…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ችሎት በስለላ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ሶስት ግለሰቦች እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ። ተከሳሾቹ ነጋሲ ብርሀነ ሹማይ፣ ተበጀ በረኸ እና ብለፅ ገብረፃድቃን በትግራይ ከልል ምስራቃዊ ዞን ጉለመዲ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌያት የሚኖሩ ናቸው። በኢትዮጵያ ላይ ጉዳት በሚያደርስ ሁኔታ ለውጭ ሀገር ጥቅም ሲሉ ከኤርትራ መንግስት የደህንነት አባላት ጋር በመገናኘት ዛላንበሳ…
‹‹በአንድ ቀን መሰጠት ያለበት ውጤት ከወር በላይ እያስቆጠረ ነው›› የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ‹‹ምንም ችግር የለብንም›› ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል በሰው እጅ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ሕይወቱ በድንገት ያለፈን ሰው አስከሬን በምርመራ (ከትግራይ ክልል በስተቀር) ለሁሉም የአገሪቱ ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል፣ የምርመራ ውጤት ሳይሰጥ ከአንድ ወር በላይ በማዘግየቱ ከአዲስ አበባ…
የሼህ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ነው የቅጣት ውሳኔውን በግለሰቡ ላይ ያስተላለፈው። ተከሳሹ ሀብታሙ ወርቁ ይሰኛል፤  በቤንች ማጂ ዞን፣ ሼህ ወረዳ ሻፑ ጉይድ ቀበሌ ውስጥ በያዝነው ወር መስከረም 6፣ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ንብረትነቷ የአቶ ጎንጣብ ይህንሳብ የሆነችውን እና ዋጋዋ 500 ብር የተገመተውን  ፍየል ጓሮ ገብታ የጫት ተክሌን በልታብኛለች በሚል ምክንያት…
ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት ሀሰተኛ ወሬዎችን አሳትሞ በማሰራጨትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ በሚል ክስ የቀረበባቸው ሶስት መፅሔቶች እና የድርጅቶች ስራ አስኪያጆች ጥፋተኛ ተባሉ። ጥፋተኛ የተባሉት አዲስ ጉዳይ መፅሔት እና  የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ፣ ሎሚ መፅሔትና የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ፣ ፋክት መፅሔትና ስራ አስኪያጅዋ ፋጡማ…
-  ከደቡብ አፍሪካው አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሏል ጀሃዳዊ ጦርነት በማወጅና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን በማናጋት እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል ተብለው፣ ከዓመት በፊት በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር ላይ በነበሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ መስከረም 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በኦሮሚያ ክልል ጅማና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ነዋሪ መሆናቸው በክሱ…
በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል በመዠንገር ዞን ውስጥ የተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ ተብለው የተጠረጠሩ 15 የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ኃይል በቅንጅት ባደረጉት ምርመራ ለብጥብጥ ዋነኛ ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ 15 የሥራ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ከእነዚህ ባለሥልጣናት ጋር ቁርኝት ያላቸው…
-  ክሱ ገና አልተሰማም የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ‹‹ዶ/ር ኢንጂነር›› በሚል ሐሰተኛ ማዕረግ በመጠቀም የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ የመሠረተባቸው አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል፣ በፍርድ ቤት ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ለብይን ተቀጠረ፡፡ የተጠረጠሩበት የወንጀል ክስ ዋስትና የማያስከለክል መሆኑን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ሦስት ተቃውሞዎች በማቅረብ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግለት…
-  የተጠረጠሩት ከኦሮሚያ ውኃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሒሳብ ጋር በተገናኘ ነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍና በባምቢስ ቅርንጫፍ የሚሠሩ አምስት ሥራ አስኪያጆች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡ መስከረም 16 ቀናት 2007 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ…
ፊልሙ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ከሐሙስ ጀምሮ ይታያል የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. ተገኝተው ለ15 ደቂቃዎች ከታየ በኋላ፣ በፍርድ ቤት ዕግድ ተጥሎበት የተቋረጠው ‹‹ድፍረት›› ፊልም ችግሩ በሽምግልና በመፈታቱ ዕግዱ ተነሳለት፡፡ በአንጀሊና ጆሊ ኤግዘኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰርነት የተሠራውና ሜሮን ጌትነትን ጨምሮ በርካታ…