የሠራተኛ የደመወዝ ገቢ ግብር ተሻሻለ በሚል የተለቀቀው መረጃ እውነትነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታወቀ። የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው በተቋሙ ደረጃ ገና እየታየ ያለ ረቂቅ ነው። በማማሻያው ላይ ከክልሎች የገቢ ቢሮዎች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደተተቸ እና ከዚህ በኋላም ማሻሻያ ተደርጎ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንደሚቀርብ ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ቀጥሎም ረቂቅ ማሻሻያው ወደፊት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከታቸለ በተያዘው ዓመት አጋማሽ ላይ ወይም መጨረሻ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቦ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተለቀቀ ያለው የተዛባ የአሃዝ መረጃ በረቂቅ ደረጃም ያልተዘጋጀ መሆኑን ተገልጿል፡፡