የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል መዝገብ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለማዳመጥ ቀጠሮ ያዘ

Mar 14 2014

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞው የሀገር ውስጥ ደህንነት ሰራተኛ መዝገብ ላይ የዓቃቢ ህግ ምስክሮችን ለማዳመጥ ቀጠሮ ያዘ።

የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ የቀድሞው የሀገር ውስጥ ደህንነት ሰራተኛ  አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ ወንድማቸው አቶ ዘርአይ ወ/ሚካኤል፣ እህታቸው ወ/ሪት ትርሀስ ወ/ሚካኤል እና የቅርብ ጓደኛቸውና በንግድ ስራ በሚተዳደሩት አቶ ከበደ ዱሪ ላይ 11 የተለያዩ ክሶችን መመስረቱ ይታወሳል።

ከእነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ፤ ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት ማፍራትና በታክስ ስወራ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ግብሰቡ በግብርአበርነት  ከተከሰሱት ቤተሰቦቹ ጋር በመሆን የአቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ አቅርበው የነበረ ሲሆን ፥ የአቃቤ ህግ ሌላ መቃወሚያ በማቅረቡ ችሎቱ የተከሳሾቹን የክስ መቃወሚያ አብዛኛውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።

የ11ኛው ክስ ግን ከ10ኛው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው በሚል ክሱ ውድቅ እንዲደረግላቸው የጠየቁ ሲሆን ፥ ችሎቱም  አቃቤ ህግ በዚሁ 11ኛው ክስ ላይ ማሻሻያ እንዳይደረግ ብይን ሰጥቷል።

አቃቤ ህግ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ፅ/ቤት በኩል የክስ ማሻሻያ ነው ያለውን ያቀረበ ቢሆንም ችሎቱ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው 11ኛው ክስ ባለፈው ጊዜ ከነበረው ክስ የተለየ ነገር የለውም ብሏል።

ስለሆነም አቃቤ ህግ በቀጣይ ከሚያቀርባቸውና ከሚያስደምጣቸው ማስረጃዎች በመነሳት የክሱን ሁኔታ ተመልክቶ ውሳኔ እናስተላልፋለን ሲል ወስኗል።

ተከሳሾቹ በክሱ ላይ  መቃወሚያ እንዳላቸው ሲጠየቁም  በክስ ላይ መቃወሚያ የለንም ፤ ጥፋተኛም አይደለንም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ፤ ተከሳሾቹ ወንጀሉን አልፈፀምንም ብለው ቢክዱም ፥ ድርጊቱን የሚያስረዱ ምስክሮች ስላሉን ቀርበው ይደመጥልን ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል ፤ 10 ምስክሮችን እንዳሉት በመጥቀስ። 

ችሎቱ ለሚያዚያ 30፣ 2006 ዓ.ም የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለማዳመጥ ቀጠሮ ይዟል።

Read 38337 times Last modified on Mar 14 2014
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)