የቅጅ መብት ጥሰት የፈፀሙ 450 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Fanabc Mar 04 2014

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት አዲስ አበባን ጨምሮ በስምንት ከተሞች የቅጅ መብት ጥሰት የፈፀሙ 450 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ገለፀ።

ፅህፈት ቤቱ እርምጃው የተወሰደው ባለፉት ጊዜያት ባደረኩት ጥናት ላይ በመመስረት ነው ብላል። በዚህም  423 ኮምፒውተሮች፣ 336 ሚሞሪ መጫኛና 35 ሺህ ሲዲዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአዳማ ከተማ አራት ትላልቅ የማባዣ ማሽኖችና ሁለት የስቲከር መለጠፊያ ማሽኖችንም ተይዘዋል።

የፅህፈት ቤቱ  ዋና ዳሬክተር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በሲዲ የሚደረገው የቅጅ መብት ጥሰት እየቀነሰ ቢመጣም በፍላሽና በሚሞሪ የሚደረገው የቅጂ መብት ጥሰት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

የቅጅ መብት ጥሰት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ከዚህ ቀደም ከሚደረገው የዘመቻ ስራ ለመውጣት በመደበኛ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት።

የቅጂ መብት ጥሰት ደንቡን ማጠናክር የሚችል አዲስ ህግም በዝግጅት ላይ  ነው።

Read 33918 times Last modified on Mar 04 2014