አቶ ቃሲም ፊጤና ግብረ አበሮቻቸው ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ

Feb 25 2014

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት አስተዳደር እና የግንባታ ፈቃድ ባለስልጣንየቀድሞው ስራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም ፊጤና በሙስና ተጠርጥረው  የተከሰሱት ሶስት ግብረ አበሮቻቸው ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ።

ጉዳዩን እየተመለከተ የሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት ከከሳሽ የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ተከትሎ ከጠበቆች የተነሳውን ተቃውሞ በማገናዘብ ዛሬ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ ነበር

በዚህም አቃቤ ህግ ያቀረበው ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ ክሱን ይበልጥ ያጠናክርልኛል ብሎ ሲያቀርብ  የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው፥ የአቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበው ከተጠናቀቁ በኋላ ተጨማሪ ማስረጃ አለ በመባሉ ነው ቅዋሜያቸውን ያሰሙት።

ችሎቱ ተጨማሪ የተባለውን ሰነድ መርምሮ  በዛሬ ውሎው ማስረጃው የፍትህ ስርዓቱን ከማገዙ በቀር ጉዳት የለውም በማለት በተጨማሪነት ይዟል።

በክስ መዝገቡ ላይ አጠቃላይ የአቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመጠናቀቁ በተጨማሪ ሰነዱ ላይ አስተያየት ካለ እንዲቀርብ በማዘዝ፥ ተከሳሾች ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን በመስጠት ፍርድ ቤቱ ለመጋቢት 18፣ 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Read 37455 times Last modified on Feb 25 2014
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)