አቶ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ የክስ መቃወሚያ ለማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ ጠየቁ

Feb 06 2014

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ የክስ መቃወሚያቸውን ለማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

የፈደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎትም ሁለቱን ተከሳሾች ጨምሮ ሌሎች መቃወሚያ ለማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቁ ተከሳሾች ለየካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ውሳኔ አስተላልፏል።

በ3 መዝገብ የሰፈሩ በርካታ ተከሳሾች ደግሞ መቃወሚያቸውን ዛሬ ለችሎቱ በፅሁፍ አቅርበዋል።

ችሎቱ እስከዛሬ ያልቀረቡት አቶ ታደሰ ፈይሳ ፣ ገዳ በሸር ፣ ጌቱ ገለቴ እና ነጋ ቴኒ የተባሉ ተከሳሾች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልቀረቡ በመሆኑ ፤ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይም ነው ዛሬ ውሳኔ ያስተላለፈው ።

በሌላ ጉዳይ ችሎቱ የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ በነበሩት የነአቶ ወልደ ስላሴ ወልደ ሚካኤል መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው አራት ተከሰሻች ጉዳይንም ተመልክቷል።

እነዚህ ተከሳሾች ምንጩ ያልታወቀ ሃብት ማፍራትና ይዞ መገኘት የሚለው ከተመሰረተባቸው ክሶች ውስጥ ይጠቀሳል።

በዚህ መዝገብ ላይ አቃቤ ህግ የክስ ማሻሻያ ለማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት ችሎቱ  ለየካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

Read 36949 times Last modified on Feb 06 2014
Abyssinia Law | Making Law Accessible!

Abyssinia Law is  a legal resource portal providing open access to primary and secondary legal materials for Ethiopia, such as laws, court decisions, articles, contact guidance and Lawyers Directory - with texts supplemented by online videos, a discussion forum and user blog. The service gives free access to Federal and State consolidated laws of Ethiopia (with status information whether the law is amended, repealed or effective)