- Details
- Category: Matters that need enactment - ሕግ ሊወጣላቸው የሚገቡ ጉዳዮች
ባለንበት ዘመን ሕገ መንግሥት ወይም ስለመንግሥት አሠራርና አመራር የሚደነግግ ሕግ የሌሎው ሀገር ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ ሳስበው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መደንገግና በዛው ልክ መቆጣጠር ያስፈለገበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ ካለፈባቸው የችግርና የጦርነት ውጤት የቀሰመው አብይ መፍትሔ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ አብዛኞቹ ሀገራት በሕገ መንግሥታቸው ውስጥ ከሚያካትቱት መሠረታዊና ጥቅል ድንጋጌዎች መካከል የመንግሥት ሥልጣንና ተግባር፣ የዜጎች መሠረታዊ መብትና ግዴታ፣ የመንግሥት አስተዳደርና የሥልጣን ክፍፍል እንዲሁም የአሠራር ሁኔታ ይገኙበታል፡፡
- Liku Worku By
- Hits: 12635