ምትክ ዳኞች ስለሚሾሙበት እና ስለሚሰሩበት ሁኔታ - የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 132 - 135
የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ከቁጥር 132 እስከ 135 ድረስ ምትክ ዳኞች /Judicial Commissioners/ በፍርድ ቤቶች ስለሚሾሙበት፣ የሥራ ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን ያስቀምጣል፡፡ ለመሆኑ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ምትክ ዳኞችን አስመልክቶ የሚያስቀምጣቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው? ለተከራካሪ ወገኖች የምትክ ዳኞች መሾም አስፈላጊነቱ ምንድን ነው? ሕጉ በተግባር እየተፈፀመ ነው ወይ? የሚሉና ሌሎች ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡