በ2001 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት በመሆን ተሹመው ለሰባት ዓመታት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትነት ሲያገለግሉ የቆየቱት አቶ ተገኔ ጌታነህ ሥራቸውን በፈቃዳቸው ከሥራቸው የለቀቁ መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ገለጸ፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንቱ ከሳምንት በፊት መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የመልቀቂያቸው ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ መሆኑን በደብዳቤያቸው እንዳሰፈሩ ተገልጻል።
ይህ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ በጤንነት ያሳቡ እንጂ በመልካም አስተዳደር ላይ የተንሰራፋው ችግር አለመፈታት ከሥራቸው ለመነሳት ምክንያት ነው የሚሉ ጉዳዩን በቅርብት የሚያውቁ ገልጸዋል ሲል ፎርቹን ገልጻል፡፡ በሌላ በኩል የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ውብሸት ሽፈራው መነሳትም ከጉዳዩ ጋር እንደሚገናኝም የሚገልጹ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎችም አልጠፉም፡፡
በኢሉባቡር ዞን በመቱ የተወለዱት እና ለጡረታ ጥቂት ጊዜ የቀራቸው አቶ ተገኔ ጌታነህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ከመሆናቸው በፊት የከፍተኛ እና የጠቅላይ ፍርድቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል፡፡