Draft Laws

Draft Laws

በዚህ ክፍል ረቂቅ አዋጆችና ደንቦችን እናቀርባለን፡፡ ዓላማውም ሕጉ ከመውጣቱ በፊት  የሕግ ባለሙያዎች ልዩ ልዩ ሐሳቦቻቸውን እና አስተያየቶቻቸውን እንዲያቀርቡ ማስቻል ነው፡፡

  አዋጅ ቁጥር ---/2012 የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት መንግስታዊ አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበትና ማናቸውም የመንግስት ባለሥልጣን ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን የተመለከተ በመሆኑ፤ ዘመናዊ መንግሥት ከጊዜ ወደ ጊዜ ልዩ ልዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን የመስጠት ተግባሩን እያስፋፋ በመምጣቱ ምክንያት በአስተዳደር ተቋማቱ በኩል ከዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት መፍጠሩ በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትለው ጣልቃገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ የሚገዛ መሆኑን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤ የአስተዳደር ተቋሞች በሕግ የተሰጣቸውን አስተዳደራዊ ውሳኔ የመስጠት እና መመሪያ የማውጣት ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ…
አዋጅ ቁጥር ........./2011 የሕግ አገልግሎትን ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ሉላዊነት በጥበቅና ሙያ ቁጥጥር እና በተቆጣጣሪው አካል ላይ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት በመደቀኑ፤ ተቆጣጣሪ አካላቱ ለእነዚህ ተግዳሮቶች የሚሰጡት ግብረ መልስ የተለያየ በመሆኑ እና አብዛኛውን ጊዜ በአንድ አገር የሚደረገው ቁጥጥር በሌላ አገር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ፤ የኢትዮጵያ የሕግ መሠረተ ልማት ከአገሪቱ ፈጣን የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ሥርነቀል ለውጥ አንጻር ኋላ ቀር መሆኑን በተገቢው ሁኔታ በመገንዘብ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በሥራ ላይ ያሉትን ሕጎች እና የሕግ ተቋማት መልሶ ለማዋቀር እና ለማሻሻል መሠረታዊና መጠነ ሰፊ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆኑ፤ በሌሎች የሕግ…