ሰበር ሰሚ ችሎት አንድን ጉዳይ ለማቅረብ መረጋገጥ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንድ የስር ፍርድ ቤት ሰነዶች ይገኝበታል፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩ ከወረዳ፤ ከማህበራዊ  ፍርድ ቤትወይም ከመጀመሪያ /ቤት ወይም ከከፍተኛ ፍ/ቤት ወይም ከክልል ጠቅላይ /ቤት ወይም ከክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተነሳ በጉዳዩ ቅር የተሰኙበት ውሳኔው /የውሳኔ ሰነዱ/

  1. ቀኑ እና የፋይል ቁጥሩ የሚነበብ
  2. የተሰየሙ ዳኞች ስም ያለው
  3. የተከራካሪ ወገኖች ስም ያለው

መሆኑን በትክክል ያረጋግጡ!

 

የውሳኔ ሰነዱ ከላይ የተገለጹትን ነገሮች ሟሟላቱን ካረጋገጡ በኋላ በሁሉም ውሳኔዎች ወይም የውሳኔ ሰነዶች ላይ የየፍ/ቤቱ ማኅተም በግልጽ የሚታይና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆኑን ማረጋገጥ አይዘንጉ፤ በተጨማሪ የመጨረሻው ፍርድ ቤት የሰጠው መሸኛ መሠረት በማድረግ የገፆች ብዛት እንደየ ፍርድ ቤቱ ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም የፍ/ቤቶቹ ውሳኔዎች በግልጽ የሚነበቡና ተከታታይነት ያላቸው መሆናቸው አረጋግጠው ማቅረብ አለብዎት፡፡

 

የውሳኔ ሰነዶቹ ትክክለኛ መረጃ እና መኅተም መያዛቸውን ካረጋገጡ በኋላ የመጨረሻው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 90 ቀን በመቁጠር ጳጉሜን ጨምሮ ቀኑ ያላለፈበት መሆኑን ማረጋገጥ አለበዎት፡፡ ውሳኔው ከተሰጠ 90 ቀን ያለፈው እንደሆነ ከሕግ ባለሙያ ጋር ተነጋግረው የማስፈቀጃ ጥያቄ እንዲያቀርብ ማድረግ ይኖርበዎታል፤

 

የሰበር ቅሬታውን ወይም አቤቱታውን የሚያመለክቱት ራስዎ /በግልዎ/ ከሆነ ቅሬታው (አቤቱታው) ላይበሁሉምገጾች ላይመፈረምዎን አይዘንጉ! የሰበር ቅሬታውን ወይም አቤቱታውን የሚያቀርቡት ማረሚያ ቤት ሆነው እንደሆነ (አቤቱታው) ላይ ከርሶ ፊርማ በተጨማሪ የማረምያቤቱማህተምመኖሩን ያረጋግጡ፤

 

የሰበር ቅሬታዎን ወይም አቤቱታዎን በራስዎ ማቅረብ ካልቻሉና ሌላ ሰው የወከሉ እንደሆነ የተወካዩ ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ ማኖርና የውክልና ማስረጃ ማያያዝዎን አይዘንጉ! ውክልናው በአማርኛ ከሆነ የውክልና ኮፒ፣ ውክልናው በክልል ቋንቋ የተጸፈ ከሆነ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ከዋናው ኮፒ ጋር በመያያዝ መቅረብዎን አይዘንጉ! 

 

የሰበር ቅሬታዎን ወይም አቤቱታዎን በጠበቃ የሚያቀርቡ ከሆነ ጠበቃው ቅሬታው ወይም አቤቱታው ላይ መፈረሙን፣ የውክልና ማስረጃ ማያያዙን ያረጋግጡ! ውክልናው በአማርኛ ከሆነ የውክልናው ኮፒ፤ በሌላ ቋንቋ ከሆነ ደግሞ ወደ አማርኛ አስተርጉመው የአማርኛ ትርጉም በተጨማሪ የዋናው ኮፒ መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

 

ከላይ የተገየፁት ውሳኔዎች፤ ውክልና፤ የጥብቅና አገልግሎት ውል፤ የተገደደበት ወረቀት/ትእዛዝ  በክልል ቋንቋ የተጻፉ ከሆነ በሕጋዊ ትርጉም /ቤት ወደ አማርኛ ተተርጉመው ትርጎሞቻቸው መያያዝ አለባቸው፡፡