Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ለሚገኙ አስሩም ክፍለ ከተሞች ለኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲውል የተረከባቸውን የተለያዩ እቃዎች የመዘበረው የአስተዳድሩ የንግድ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ባልደረባ ዛሬ በሰባት አመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ። ወንጀለኛው በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር ክፍል ውስጥ ይሰራ የነበረ ሲሆን፥ አያሌው በቀለ ይባላል። የ42 አመቱ ጎልማሳ ሰኔ 2003 ዓ.ም ለአስሩም ክፍለ…
635 የመከላከያ ምስክሮች በተከሣሾች ተቆጥረዋልበትናንትናው እለት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞ አሰምቷልበአወሊያ ት/ቤት መነሻነት “ድምፃችን ይሠማ” በሚል ከተፈጠረው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ በእነ አቡ በከር መሃመድ መዝገብ ስር፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት 18 ግለሰቦች ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ጭብጥ ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤቱን አከራክሯል፡፡ የተለያዩ የሽብር ተግባሮች ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው ክስ የቀረበባቸው 18 ተከሳሾች፣ ቀደም…
የክልል መንግሥታት የሕዝቦቻቸውን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ረቂቅ የሕግ ማዕቀፍ እያዘጋጀ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ገለፀ። የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ፤ ለረቂቅ ሕጉ ግብዓት ለማሰባሰብ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በተዘጋጀ ዓውደ ጥናት ላይ እንደተናገሩት ፥ ድህነትና ኋላቀርነትን በማስወገድ በሚፈጠረው ልማት የሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጠናከረ…
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ደኅንነት ሠራተኛ በሆኑት አቶ ዮሐንስ ኪሮስ አብዩና በአቶ በኩረ ጽዮን አብረሃ ዜና፣ እንዲሁም ሾፌር መሆኑ በተገለጸውና ተባባሪ ነው በተባለው የኑስ አብዱልቃድር መሐመድ ላይ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ምስክሮች መስማት የጀመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት…
የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው በራያ ቆቦ ከተማ የነዳጅ ማደያ በመክፈትና ነዳጅን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ለገበያ በማቅረብ ፤ በሸማቾችና በተሽከርካሪ ንብረት ላይ ጉዳይ ባደረሰ ግለሰብ ላይ የ11 ዓመት ዕኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ። አቶ ነጋ አስገዶም የተባለው ይሄው ፍርደኛ የተባበሩት ብሄራዊ ፔትሮሊየም አ.ማ በሚል በከፈተው…
ለሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበውና ሐሰተኛ መሆኑ የተገለጸው ሰነድ በፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት ተመርምሮ ‹‹ተፈርሟል ወይም አልተፈረመም ለማለት አልተቻለም›› የሚል አሻሚ ምላሽ የተሰጠበት ቢሆንም፣ በሞግዚትነት ተሹመው ያስተዳድሩት የነበረን ያደራ ይዞታ ‹‹ከባለቤቴ የገዛሁት ነው›› በማለት እስከ ሰበር ችሎት ድረስ ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ አግኝቶ የነበረው የውርስ ይዞታ ጉዳይ፣ በሥር ፍርድ ቤት ክርክር…
ወንጀለኛው  ወንደሰን ይልማ  ጥፋቱን የፈፀመው  ባለፈው ዓመት ጥቅምት አስር ከማለዳው  ሁለት ሰዓት ላይ ነው ። በወቅቱ  የሁለት  ልጆቹ እናት የነበረችውን ሟች ወይዘሮ  ፍሬህይወት ታደሰ የግል መኪናዋን ይዛ ወደ ባምቢስ መስመር ትጓዛለች። ተከሳሽ ህጋዊ  ፈቃድ የሌለው  ክላሽ  ጠመንጃ  በግል መኪናው ውስጥ  አስቀምጦ  ይከታተላታል፤ ከዚያም በቂርቆስ  ክፍለ ከተማ  በተለምዶ ኦሎምፒያ  ካርቱም ሬስቶራንት በሚባል …
የኬንያ ፓርላማ አንድ ወንድ የሚስቱን ፍቃድ ሳይጠይቅ ተጨማሪ ሚስቶችን ማግባት ይችላል የሚል ህግ አጸደቀ የህጉን መጽደቅ የተቃወሙ ሴት የፓርላማ አባላት የጉባዔውን አዳራሽ ለቅቀው ወጥተዋል፡፡ ህጉ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሀገሪቱን የትዳር ህግ ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀና በባህላዊ መንገድ በስፋት በኬንያ የሚካሄዱ ባህላዊ ልማዶችን በህግ ማዕቀፉ ውስጥ ለማካተት የተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ረቂቅ ህጉ “ባል ተጨማሪ…
የብሔር ብሔረሰቦችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅና የልማቱ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ የብሄረሰቦች ፕሮፋይል ጥናት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በምክር ቤቱ የዴሞክራሲያዊ  አንድነትና የመንግስታት እርስ በርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ በቀለ ጥናቱ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን በምክር ቤቱ ያልተወከሉና አዲስ የብሔር ጥያቄ  ያነሱ ህዝቦችን ህጋዊ እውቅና ለመስጠት እንደሚያስችል ገልፀዋል።…
12 ዳኞች በስነ-ምግባር ጉድለት ከኃላፊነት ተነስተዋል ለበርካታ ዓመታት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ታረቀኝ አበራ አይዶ ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን ምክትላቸው የነበሩት አቶ ሙሉጌታ አጎ፤ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡ በክልሉ ከወረዳ እስከ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲያገለግሉ የነበሩ 12 ዳኞች፤ በስነ-ምግባር ጉድለት ከሃላፊነታቸው እንደተነሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ…
በየሳምንቱ ረቡዕ ማታና በድጋሚ ቅዳሜ ላለፉት 127 ሳምንታት በመተላለፍ ላይ ካለው ‹‹ሰው ለሰው›› ድራማ የሚገኘው ማንኛውም ዓይነት ገቢ ለማንም እንደይከፈል፣ መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በፍርድ ቤት ዕግድ ተጣለበት፡፡ ክፍያው እንዳይፈጸም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግልግል ዳኞች ክልከላ የተጣለባቸው፣ አቶ መስፍን ጌታቸው (በአሁኑ ጊዜ የድራማው ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተር) አቶ ሰለሞን…
-የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ላይ ምላሽ ሰጠ በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል ላለፉት አሥር ወራት በእስር ላይ የሚገኙት፣ በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ታዋቂ ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና አርሶ አደሮች ለብይን…
በሐረር ከተማ ሰሞኑን የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ አጋጣሚ በመጠቀም ስርቆት የፈጸሙ አራት ተከሳሾች ላይ አንድ ዓመት ከ10 ወር እስከ አራት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን የክልሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አስታወቀ። የመጀመሪያ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ወይዘሪት ሁዳ አብዱረሓማን እንደገለጹት ተከሳሾቹ ቅጣቱ የተወሰነባቸው በከተማው ሲጋራ ተራ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት…