Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

ፖሊስ ሌሎች ያልተያዙ አሉ ብሏል ተጠርጥረው በተያዙት ሦስት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ላይ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተጨማሪ የአሥር ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ካዋለችው የ‹‹ዞን ናይን›› ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል ስድስቱን በሁለት መዝገብ ከፍሎ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት…
በትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርን ጨምሮ አስር የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ። ተከሳሾቹ ሻምበል ከበደ አስረስ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የአስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር፣ ወይዘሮ የሺዓለም አምባው አለኸኝ የኢንስቲትዩቱ ገንዘብ ያዥ፣ የኔነሽ ሃይለማሪያም ገንዘብ ያዥ፣ አረጋኸኝ ኩማ ሃይሌ የዕቃ ግዥ ሰራተኛ፣ ጋሻው ዘውዴ ወርቁ ንብረትና…
የግል ድርጅቶችን የስራ ሁኔታን የሚቆጣጠሩ  የስራ ሃላፊዎች የሚጠየቁበት የስነምግባር ደንብ ስራ ላይ ሊውል ነው። የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዋጅ ከ10 ሰራተኞች በላይ ቀጥረው የሚያስተዳድሩ የግል ድርጅቶች እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ነው ተደራሽ አድርጎ የሚሰራው ። እነዚህን በሀገሪቱ የሚገኙ ድርጅቶች የስራ ሁኔታ የሚከታተሉ ተቆጣጣሪዎችም ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፎች  ተደራጅተዋል። ይሁንና በዘርፉ የተሰማሩ…
የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ይቅርታ የማያሰጡ የወንጀል ዓይነቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽ ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ፡፡ ሌሎች ማስተካከያዎች የተካተቱበት ይህ የይቅርታ አዋጅ ባለፈው ማክሰኞ ፀድቋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ ክፍል ሦስት አንቀጽ 14 ንዑስ አንድ በሕገ መንግሥቱ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ተብለው ከተቀመጡት ወንጀሎች በተጨማሪ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ወይም የማይጠየቅባቸው በማለት ከአሥር በላይ ወንጀሎችን…
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የቀረቡ 63 ዕጩ ዳኞችን ሹመት ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡ የተሿሚ ዳኞቹ ቁጥር የበዛው የፍትሕ ሥርዓቱን የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡ የሕግ መምህራንን በመመልመልና በማሠልጠን ለዕጩ ዳኝነት እንዲበቁና እንዲሾሙለት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማቅረብ ሕጋዊ ኃላፊነት የተሰጠው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ነው፡፡ ጉባዔው…
የፌደራሉ ከፍተኛ  ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር  የመሬት አስተሰዳደር ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን የቀድሞ ስራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም ፊጤ ተከሰው የነበረበትን የሙስና ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ  እንዲሰናበቱ ወሰነ። ተከሳሾቹ አቶ ቃሲም ፊጤን ጨምሮ  የሊዝ አሰባሰብ ክትትል ባለሙያ አቶ ገብረየስ ኪዳኔ፣ የመሬት አቅርቦት አፈፃፀም ንዑስ የስራ ሂደት መሪ በቀለ…
በተለያዩ ምክንያቶች ለመካንነት የተዳረጉ ሴቶች በሰው ሰራሽ መንገድ መውለድ እንዲችሉ የሚፈቅድ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ። አገሪቱ በሰው ሰራሽ መንገድ መሃን የሆኑ ሴቶች ልጅ እንዲያገኙ ስራው በህግ የተደገፈ እንዲሆን የተለያዩ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰሰ ደንብ ስታዘጋጅ ቆይታለች። ደንቡም ከሳምንታት በፊት በሚኒስተሮች ምክር ቤት ጸድቋል። ይህን ደንበ ማጽደቀ ያስፈለገው ልጅ ማግኘት…
አዲስ ደንበኛ ለሆኑዋቸው የአክሰስ ሪል ስቴት ተጐጂዎች ጠበቃ በመሆን፣ በቀድሞ ደንበኛቸው ላይ ክስ መሥርተዋል የተባሉ የሕግ አማካሪና ጠበቃ የጥብቅና ፈቃዳቸው ለሁለት ዓመት ታገደ፡፡  በጥብቅና ፈቃዳቸው ላይ ለሁለት ዓመት እግድ የተጣለባቸው ጠበቃ አቶ ሲሳይ ተፈራ ናቸው፡፡ እግዱን የጣለባቸው በፍትሕ ሚኒስቴር የጠበቆች ፈቃድና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን፣ የእግድ…
-ክፍለ ከተማው ለሕግ ተገዥ አለመሆኑ ትልቁ ሥጋት መሆኑም ተጠቁሟል  የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲና የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት በተደጋጋሚ የደረሳቸውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊቀበሉ ባለመቻላቸው፣ የአስተዳዳሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ጥብቅ ትዕዛዝ ደረሰው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣…
ስድስት የሚሆኑት በመሠረቱት ክስ አሸናፊ ሆነው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለጨረታ ቀርቦ 39 ሚሊዮን ብር የተሸጠው የአክሰስ ሪል ስቴት ይዞታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታገዱ ተሰማ፡፡ ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት በመግለጽ ክስ መሥርቶ የሚገኝውን ጋቢ ኢንቨስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች፣ አክሰስ ሪል ስቴት ያደረሰባቸውን በደል በመግለጽ በፌደራል…
ቅርሶችን በብሄራዊና በክልል ቅርስነት መመደብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ።  የሀገሪቱ ቅርሶች ከብዛታቸው የተነሳ የማስተዳደሩ ስራ በመንግስት አካል ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ ፣ በዘላቂነት ጥበቃ የሚያደርግላቸው አካል በህግ መወሰኑ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱና የፌድራልና የክልል መንግስታት ቅርሶች አስተዳደር ያላቸውን ድርሻ መለየት አስፈላጊ መሆኑ አዋጁን ለማውጣት ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። በአዋጁ የሀገሪቱ የቅርስ ሀብት በብሄራዊና…
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት  4ኛ ወንጀል ችሎት ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሽብር ተግባር ወስጥ ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ከተከሰሱት ግለሰቦች መካከል የ8ኛ ተከሳሽ መሀመድ አባተና የ9ኛ ተከሳሽ አህመድ ሙስጠፋን የተከሳሽነት ቃላቸውን ትናንት አድምጧል። 8ኛ ተከሳሽ መሀመድ አባተ ሐምሌ 7 2004 ዓ.ም በአንዋር መስጊድ ለተሰበሰበው ህዝብ በአውሊያ መስጊድ ፖሊስ ሙስሊሞችን ስለገደለ ለሟቾች ፀሎት…
ባለቤቱን ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታደሰን በአሥር ጥይቶች ደረቷን፣ ጭንቅላቷን፣ ግንባሯን፣ ሆዷን፣ ጀርባዋን፣ ሁለት ታፋዎቿን፣ እጆቿንና የተለያዩ የሰውነት ክፍሏን በመምታት ጭካኔ በተሞላበት የግፍ አገዳደል ፈጽሟል በሚል፣ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ተፈርዶበታል፡፡ ግለሰቡ ተመሥርቶበት በነበረው ሰባት ክሶች በሁሉም ጥፋተኛ በመባሉ በድምሩ 81 ዓመታት ከስድስት ወራት የሚያስቀጣው ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሕግ ከ25…
-በፕሮግራሙ ያስተላለፈውን ስም አጥፊ ዘገባ እንዲያርም ታዟል የኢትዮጵያ ሬዲየና ቴሌቪዥን ድርጅት ከኅዳር 16 እስከ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. በተከታታይ ሦስት ክፍሎች ‹‹አኬልዳማ››  በሚል ባቀረበው ዘጋቢ ፕሮግራም፣ ክብርና ዝናን የሚያጠፋ በድምፅ፣ በምስልና በጽሑፍ በተቀነባበረ መንገድ ስሙን እንዳጠፋው በመግለጽ፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በመሠረተበት የፍትሐ ብሔር ክስ ተረታ፡፡  የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ…