Legal News - የሕግ ዜናዎች

Legal News - የሕግ ዜናዎች (301)

Abyssinia Law is the Ethiopian's leading legal news and information network for lawyers and other legal professionals. Read up-to-date legal news including civil trials, guilty verdicts and plea deals. 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንጃ ማህበረሰብ ብሄረሰብ ለመሰኘት የሚያበቃ መመዘኛ አያሟላም በማለት የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አጸደቀ። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የመንጃ ማህበረሰብ  የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረበውን ይግባኝ ተከትሎ ነው። የመንጃ ማሀበረሰብ አባለቱ ማንነታችን ልዩ ነው ይህም እውቅና ይሰጠው…
የተያዘው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሲመለከት ነው በወሰን ግጭት ምክንያት የሦስት ሕፃናትን ወላጆች በጥይት ደብድቦ በመግደል ወንጀል ታስሮ ከነበረበት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም. አምልጦ የነበረው ተጠርጣሪ፣ ግንቦት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያንና የጋናን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ሲከታተል መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ አቶ ዳንኤል…
የተከሳሾች መቃወሚያ ውድቅ ሆኗል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛ ወ/ችሎት የሙስና ክስ የቀረበባቸውን የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታንና በሶስት መዝገቦች የተከሰሱ ሌሎች ተከሳሾችን የክስ መቃወሚያና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በትናንትናው እለት ብይን ሰጠ፡፡ ፍ/ቤቱ አብዛኛውን የተከሳሾችን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል፡፡ ፍ/ቤቱ ብይኑን ከመስጠቱ በፊት ተከሳሾቹ ያመለከቱትን የክስ መቃወሚያና የአቃቤ…
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ታኅሳስ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ካካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ጋር በተያያዘ በኅብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ታኅሳስ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ተጽፎ በተመሠረተበት ክስ በመረታቱ፣ የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔና ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ተሻሩ፡፡ የኅብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ከፍተኛ ባለድርሻና የቦርድ ሊቀመንበር፣ እንዲሁም የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር…
ከልደታ ምብድ ችሎት ወደ አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት ተዘዋውሮ ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ብይን ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው የእነአቶ መላኩ ፈንታ የክስ ጉዳይ፣ የችሎቱ አዳራሽ በመጥበቡ ምክንያት ለግንቦት 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀየረ፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፈው አንድ ዓመት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፈንታንና አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ፣…
“የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም መሳካቱን ወይም አለመሳካቱን ለማወቅ መለካት አለበት” ዶ/ር መንበረ ፀሐይ ታደሰ፣ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር  በመንግሥታዊ ተቋማት ተግባራዊ የሚደረጉ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መሆን አለመሆናቸውንና በተቋማቱ ውስጥ መኖር አለመኖራቸውን እንዴት ማወቅ እንደሚቻል፣ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና ለአምስት ቀናት የሚቆይ የአገር ውስጥና የውጭ ኤክስፐርቶች የሚወያዩበት  ዓውደ ጥናት ከግንቦት…
‹‹ከተደጋጋሚና አሰልቺ ‘አባል ነህ?’ ጥያቄ ውጪ ምንም አልተጠየቅንም›› ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች በህቡዕ በመደራጀት፣ ሥልጠና በመውሰድና በውጭ ከሚገኙ አሸባሪዎች ጋር በመገናኘት የአመፅ ወንጀል ለመፈጸም ሲቀሳቀሱ ነበሩ ተብለው የተጠረጠሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን ላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ ትዕዛዞች ሰጠ፡፡   በቁጥጥር ሥር ከዋሉ 26 ቀናት ያስቆጠሩት ተጠርጣሪዎቹ ለሦስተኛ ጊዜ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ…
-በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦችና ንብረቶች ታግደዋል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከመሬት ባለይዞታነት ጋር የተገናኘ ሙስና ፈጽመዋል ብሎ በጠረጠራቸው 12 ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሠርት መሆኑን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክት ቤት ባቀረበው የ10 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደገለጸው፣ ሐሰተኛ የመሬት ባለይዞታነት መረጃ በማዘጋጀትና ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታ ላላሟሉ ሰዎች የመንግሥት መሬት አላግባብ…
የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች ላይ ይግባኝ ተጠየቀ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ በማለት ሕገወጥ ኮሚቴ አቋቁመውና የእምነት ነፃነትን የሚቃረን፣ ከራሳቸው አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጪ፣ ሌላ እምነትም ሆነ አስተምህሮት እንዳይኖር የሃይማኖት አስተማሪዎች ቡድን በህቡዕ አቋቁመው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል በሚል ተጠርጥረው የታሰሩት፣ እነ አቡበከር አህመድ መሐመድ (18 ሰዎች) የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ከግንቦት…
-በቀድሞው የደኅንነት ኃላፊና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ምስክር መስማት ተጀመረ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንድ ዓመት ያለፋቸው የእነ አቶ መላኩ ፈንታ ክስ፣ ከሌሎች የክስ መዝገቦች ተለይቶ ሊታይ መሆኑን ፍርድ ቤት ሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ የተጠርጣሪዎቹን ክስ በመመርመር ላይ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት…
የትግራይ ክልል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀምና በሙስና ወንጀል ይከሰሳቸውን አራት ግለሰቦች እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ቀጣ። ተከሳሾቹ አቶ አብዱልቃድር ኢብራሂም ሁሴን ፣ አቶ ጎይቶም አሰፋ ልጃለም ፣ አቶ ደሱ ሀለፎም ወዳጀ ፣ አቶ ሙሀመድ ብርሀን ሙሀምድ የተባሉ ናችው። 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በወልቃይት ወረዳ የውሀ…
ሁለት ጦማሪያን መደብደባቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ ‹‹ግብረ አበሮቻቸውን መያዝና የምስክሮች ቃል መቀበል ይቀረናል›› የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ‹‹ችሎቱ ጠባብ ስለሆነ እንጂ ጉዳዩ የሚታየው በግልጽ ችሎት ነው›› ፍርድ ቤት በህቡዕ ተደራጅተው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ካሉ አሸባሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ኅብረተሰቡንና መንግሥትን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ጠበቆች፣…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ የወንጀል ችሎት በእነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገቦች ለብይን የተያዘው ቀጠሮ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ። አቶ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ በ37 የክስ መዝገቦች 66 የሚጠጉ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ አቅርበው ከሳሽ አቃቢ ህግም ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል። ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ተቃውሞ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር…
-የኦሮሚያ አንድ ቢሮና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም ተታለዋል የሕንፃ ተቋራጭነት ሙያ ሳይኖራቸው የማይገባ ብልፅግና ለማግኘት፣ ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብና ሙያ እንዳላቸው በማስመሰል ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማሳየት፣ ከቻይናው ሲጂሲ ኦቨርሲስ ጋር ውል በመዋዋል፣ ከአንድ ግለሰብ አንድ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በማታለል ወስደዋል የተባሉ ተጠርጣሪ…