የሼህ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ነው የቅጣት ውሳኔውን በግለሰቡ ላይ ያስተላለፈው።
ተከሳሹ ሀብታሙ ወርቁ ይሰኛል፤ በቤንች ማጂ ዞን፣ ሼህ ወረዳ ሻፑ ጉይድ ቀበሌ ውስጥ በያዝነው ወር መስከረም 6፣ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ንብረትነቷ የአቶ ጎንጣብ ይህንሳብ የሆነችውን እና ዋጋዋ 500 ብር የተገመተውን ፍየል ጓሮ ገብታ የጫት ተክሌን በልታብኛለች በሚል ምክንያት በህይወት እያለች ምላሷን ቆርጦ በመብላት ወንጀል ተከሶ ነው ቅጣቱ የተላለፈበት።
ተከሳሹ ድርጊቱን ሲፈፅም የተመለከቱ የአይን እማኞች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ የተያዘው ግለሰቡ፥ የፈፀመው ወንጀል በሰው ማስረጃ በመረጋገጡ የወረዳው ፍርድ ቤት ሰሞኑን ባስቻለው ችሎት የ3 ወራትና የ300 ብር የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አስተላልፎበታል።