23 April 2014 Written by  FanaBC

ቅርሶችን በብሄራዊና በክልል ቅርስነት መመደብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

ቅርሶችን በብሄራዊና በክልል ቅርስነት መመደብ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ። 

የሀገሪቱ ቅርሶች ከብዛታቸው የተነሳ የማስተዳደሩ ስራ በመንግስት አካል ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ ፣ በዘላቂነት ጥበቃ የሚያደርግላቸው አካል በህግ መወሰኑ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱና የፌድራልና የክልል መንግስታት ቅርሶች አስተዳደር ያላቸውን ድርሻ መለየት አስፈላጊ መሆኑ አዋጁን ለማውጣት ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በአዋጁ የሀገሪቱ የቅርስ ሀብት በብሄራዊና በክልል ቅርስነት እንዲመደቡ የተደረገ ሲሆን በብሄራዊ ቅርስነት ለሚመደቡ 9 መስፈርቶችም ተቀምጠዋል።

በብሄራዊ ቅርስነት ስለሚመደቡ ቅርሶች ሃሳቦችን እየመረመረ ለውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ የቅርስ ምደባ ምክር ቤትም በአዋጁ ተቋቁሟል።

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ ውሎው ፤ ረቂቅ አዋጁን በአበላጫ ድምጽና በአንድ ድምጸ ተአቅቦ አጽድቆታል።

Last modified on Wednesday, 23 April 2014 11:35