Saturday, 12 November 2022
  1 Replies
  641 Visits
-2
Votes
Undo
  Subscribe
ባልና ሚስት በባህል ተጋብተው በ 1989 አመተ ምህረት አንዲት ሊጅ ወልደው ተፋትተዋል። ሚስት ልጇን ብቻዋን አሳድጋለች፤ ባልም ሌላ ትዳር መስርቶ ልጆችን አፍርቷል። እናት ልጇን ስታሳድግ በጥረቷ ንብረት አፍርታ ቤትም ሰርታለጭ። በ 2008 አመተ ምህረት ይህ ሰው ያኛዉን ትዳሩን አፍርሶ እና በጠና ታሞ ከመጀመሪያ ባለቤቱ ጋ እርዳታሽን እፈልጋለሁ በማለት ከቤቷ ይገባል፤ የጋራ ልጅ ስለነበረቻቸዉ በርህራሄ ያስጠጉትና አስታመዉት ከዳነ በኋላ አብረው ሲኖሩ ሶስት አመታትን አሳለፉ። እናም አባት ሁልጊዜ ከቤቱ ባለኩል አድርጊኝ የሚል ጥያቄ ያቀርብላት፤ እሷም ባለመስማማት ትመልሰው ነበር። ቆይተዉ ትርፍ ቦታ ስለነበረዉ ጥቂት ዶርሞችን አብረዉ እያሉ ሰርተዋል። ሁልጊዜ ባለ እኩል ካላደረግሽኝ እያለ ፤ ካልተስማምሽም እያለ ያስፈራራትም ነበር። ከዚህ በኋላ ጥያቄዉን አልቀበለዉ ስትል፤ ከእርሷ እዉቅና ዉጪ የራሱ የሆኑ ሰወችን ይዞ ፤ ገንዘብ እንዳጋባላት እና ከቤቱ ባለቤትነት እንዳስገባችዉ የሚገልጽ ዉል ጽፎ እነዚያን ሰወች ከቤት ይዞ በመምጣት እንድትፈርምለት ይጠይቃታል። ነገር ግን በሃሳቡ ባለመስማማቷ ሳትፈርም ቀረጭ። በዚህ የተናደደዉ ሰዉየዉ ሌሊት በ ተተኳሽ መሳሪያ ያስፈራራታል። ከዚያም ቤቷን ጥላ ወደቤተሰቦቿ ትሄዳለች። ከዚያም የቤት እቃዉን ሁሉ አዉጥቶ ከወሰደ በኋላ ክስ ይመሰርትባታል። ክሱም እሱ በሌለበት ቤቱን እንደዘረፈችዉ ያስረዳል።
አሁን አብረው ያፈሩትን ሃብት ሳይቆጥር ጥራ ግራ የሰርችዉን ቤት እኩል ታካፍለኝ ብሎ ከሷት ይገኛል።
ከሙያ አንጻር የሆነ ነገር በሉኝ።
በዚህ ጉዳይ ጥብቅና የሚቆምልኝም ሰው እፈልጋለሁ!
አመሰግናለሁ
Rate this post:
Kindu Yinges Wondie set the post as Critical priority — 2 months ago
Kindu Yinges Wondie set the type of the post as  እርዳታ — 2 months ago
2 months ago
·
#38
0
Votes
Undo
ይሄን ጉዳይ መያዝ እፈልጋለው ፍላጎት ካለ። 0913093197
  • Page :
  • 1
There are no replies made for this post yet.
Submit Your Response