Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
  • Court Fee Calculator
Abyssinia Law Abyssinia Law
  • Home
  • Laws
    • Search Federal Laws
    • Regional Laws
    • Constitutions
    • Audio Legal Resources
  • Decisions
    • Cassation Decisions by Volume
    • Cassation Decisions Database
    • FFI Court Commercial Bench Decisions
  • Blog
  • Resources
    • Researches Papers
    • Policies and Strategies
    • Codes, Commentaries and Explanatory notes
    • Legal Forms
    • Bench Books
    • Human Right Documents
    • Modules and Materials
    • About Our Laws
    • Quick links
  • Study On-line
  • know your rights
  • Lawyers
  • About Us
    • Who Are We
    • Our Partners
    • Advertise with Us
    • Privacy Policy
    • Contact us
    • Professional Advice?
    • How to submit a blog post
  • login
  • Court Fee Calculator
29.May
Hits: 1960

Court Fee Calculator

This court fee calculator is based on Federal Court Fee Regulation No. 1/2017.

Court Fee Calculator


ሌሎች / FAQ

  1. አቤቱታው የቀረበው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሆነ ብር 1,000 (ብር አንድ ሺህ) ይከፈላል።
  2. አቤቱታው የቀረበው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሆነ ብር 1,500 (ብር አንድ ሺህ አምስት መቶ) ይከፈላል።
  3. አቤቱታው የቀረበው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሆነ 2,000 (ብር ሁለት ሺህ) ይከፈላል።
  4. በቤተሰብ ሕግ መሠረት በባልና ሚስት መካከል ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግን ውል በፍርድ ቤት ለማረጋገጥ የሚቀርብ አቤቱታ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ይከፈላል። ጊዜው ያለፈበት የይግባኝ ወይም የሰበር ማስፈቀጃ አቤቱታ ለማቅረብ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፈላል፡፡
  5. በግልግል ዳኝነትዳኝነት ጉባኤ በሚታይ ጉዳይ ጊዜያዊ የመጠባበቂያ እርምጃ ወይም የእግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ወይም ሌላ ትዕዛዝ ተፈፃሚ እንዲሆን ለሚቀርብ ማናቸውም አቤቱታ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ይከፈላል፡፡
  1. በደንቡ ወይም በሌላ ሕግ ከዳኝነት ክፍያ ነጻ ከተደረጉ ወጎኖች በስተቀር በፍርድ ቤት ለሚሰጡ ማናቸውም አገልግሎቶች ክፍያ መፈጸም አለበት።
  2. ከዚህ በታች ለተመለከቱት አገልግሎቶች የሚከፈለው ክፍያ እንደሚከተለው ይሆናል፦
    1. ለተከራካሪ ወገን ወይም ለምስክር መጥሪያ ለማውጣት ለእያንዳንዱ ምስክር ብር 50 (ሃምሳ ብር) ይከፈላል፡፡
    2. የፍርድ ወይም በመዝገብ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም የሰነድ ወይም የኤሌክትሮኒክስ ሰነድ በፍርድ ቤቱ ኮፒ ተደርጎ የሚሰጠው ከሆነ በገፅ ብር 5 (አምስት ብር) ይከፈላል።
    3. ከላይ ከተመለከቱት አገልግሎቶች ውጪ ከፍርድ ቤቱ ከተጠየቀ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ ከተመለከቱት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ርዕስ ሥር የተመለከተው ክፍያ እንዲከፈል ያደርጋል።
  1. በሕግ በተሰጠ ሥልጣን መሠረት በተለያዩ የአስተዳደር ተቋማት ታይተው ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች በፍርድ ቤት በይግባኝ ወይም በቀጥታ ክስ ለሚቀርብ አቤቱታ ከዚህ በታች የተመለከተው ክፍያ ይከፈላል።
    1. አቤቱታው የቀረበው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሆነ – ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)
    2. አቤቱታው በይግባኝ የቀረበው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሆነ – ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር)
    3. አቤቱታው የቀረበው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሆነ – ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር)
    4. በአስተዳደር አካል የተሰጠው ውሳኔ እንዲከለስ አቤቱታ የቀረበው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት – ብር 500 (አምስት መቶ ብር)
    5. ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት – ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)
    6. ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት – ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)
  1. አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ወይም በክርክር ሂደት ጣልቃ ለመግባት በቀረበ አቤቱታ ለሚሰጥ አገልግሎት የዳኝነት ክፍያ ይከፈላል፡-
    1. ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠን ውሳኔ አስነስቶ ወደ ክርክሩ ለመግባት ለሚቀርብ አቤቱታ – ብር 500 (አምስት መቶ ብር)
    2. ፍርድን ለመቃወም ለሚቀርብ አቤቱታ – መቃወሚያውን ያቀረበው ወገን አስቀድሞ ተከፍሎ በነበረው ክፍያ ልክ
    3. በክርክር ሂደት ጣልቃ ለመግባት ለሚቀርብ አቤቱታ የክርክሩ የገንዘብ መጠን ከግምት ሳይገባ – ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር)

ከተከራካሪ ወገኖች አንዳቸው በክርክር ሂደት ውስጥ የአቤቱታ ማሻሻል ጥያቄን ጨምሮ በሚያቀርቡት ማመልከቻ ምክንያት ሂደቱ ወደኋላ የሚመለስ ከሆነ፣ የዳኝነት ክፍያ አቅራቢው በቀድሞ ተከፍሎ የነበረው ክፍያ 10 በመቶ (አሥር በመቶ) የማይበልጥ እንዲከፍል ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

  1. ፍርድ ከተፈረደ በኋላ፣ ለማስፈፀም በቀረበ የአፈጻጸም ማመልከቻ መሠረት፣ የዳኝነት ክፍያ እንደሚከተለው ይከፈላል፦
    1. የፍርድ መጠን ከ1 እስከ 100,000 ብር – ብር 300
    2. 100,001 እስከ 200,000 ብር – ብር 500
    3. 200,001 እስከ 500,000 ብር – ብር 1,000
    4. 500,001 እስከ 1,000,000 ብር – ብር 1,500
    5. 1,000,001 እስከ 10,000,000 ብር – ብር 2,000
    6. 10,000,001 ብር በላይ – ብር 3,000
    7. በገንዘብ ሊተመኑ የማይችሉ ጉዳዮች – ብር 500
  2. በፍርድ አፋጻጸም ወቅት የተያዘ ወይም የተከበረ ንብረት ላይ መብት አለኝ የሚል አቤቱታ ቢቀርብ፣ የንብረት ወይም ገንዘብ መጠን ከግምት ሳይገባ – ብር 1,000 ይከፈላል።
  1. ለዳኝነት የተከፈለ ገንዘብ በዚህ ሁኔታ ይመለሳል፦
    1. ከሳሽ ወገን ክሱን መዝገቡ ቀጠሮ ከመያዙ በፊት ቢቋረጥ – 5% ተቀንሶ ይመለሳል
    2. ፍርድ ቤቱ ክስ መቀበል አትችልም ብሎ ቢዘጋ – 10% ተቀንሶ
    3. ከክስ መስማት በፊት ቢቋረጥ – 15% ተቀንሶ
    4. ጉዳዩ በአስማሚ በኩል ስምምነት ተደርሶ እልባት ካገኘ – በመመሪያው መሠረት ተመላሽ ይደረጋል
    5. በስምምነት ከፍርድ በፊት ቢያቋርጡ – 10% ተቀንሶ
    6. ከክስ መስማት በኋላ ክስ ቢቋረጥ – ክፍያ አይመለስም
  1. በሌሎች ሕጎች የተደነገጉት እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ክፍያ አይከፈልም፦
    1. የተለብ ክፍያና የልጅ አስተዳደግን አስመልክቶ የሚቀርብ አቤቱታ
    2. በሴቶች፣ በሕጻናት፣ በአረጋዊያን፣ ኣካል ጉዳተኞችን እንዲሁም ሌሎች ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚቀርብ የሕዝብ ጥቅምን ለማስክበር ወይም አካልን ነጻ ለማውጣት እና ሌሎች የወል ሰብዓዊ መብታቸውን ለማስክበር በሲቪል ማኅበራት አማካይነት የሚቀርብ ክስ፤
    3. የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤን በሚመለከት የሚቀርቡ ጉዳዮችን፤
    4. በሕግ አግባብ በድሃ ደንብ እንዲከራከር በፍርድ ቤት የተወሰነለት ሰው
    5. በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክርክር
    6. አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት አንድ ሠራተኛ በግሉ በአስተዳደር አካል የተሰጠው ውሳኔ በፍርድ ቤት እንዲከለስለት ለሚያቀርበዉ አቤቱታ
×

Copyright © 2025 Abyssinia Law | Making Law Accessible! . All Rights Reserved.
Maintained by Liku Worku Legal Service