በዚህ በኩል ግቡ
ብድር የሰው ልጅ እና ጎደሎው ከተገናኙበት ሩቅ ዘመን ጀምሮ የነበረ ሰዋዊ ድርጊት ነው፡፡ የብድር መሰረቶቹ መቀራረብ፣ እዝነት እና መተማመን ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን እነዚህ መሰረቶቹ እየተናጉ የብድርን ህልውና ሲፈታተኑት ይስተዋላል፡፡ በርካታ ሰዎችም ብድርን መሰረት ላደረጉ ክርክሮች ሲዳረጉ ይታያሉ፡፡
ከእነዚህ በርካታ ብድር ነክ ክርክሮች አንዱ በውሉ ላይ ተበዳሪ ተብለው የተሰየሙ ሰዎች የብድሩን ገንዘብ አልተቀበልኩም በማለት የሚያነሱት ክርክር ነው፡፡ ተበዳሪው በውሉ ላይ ተበድሬአለሁ ብሎ የፈረመ ቢሆንም ውሉ ፍ/ቤት ሲመጣ ግን ተበድሬአለሁ ብዬ ፈርሜአለሁ ግን የብድሩን ገንዘብ አልተቀበልኩም ማለት ይከራከራል፡፡