In different legal systems of the world, properties are classified into different categories such as personal and real, private and public, movable and immovable, absolute and qualified, corporeal and incorporeal, etc. The distinction between these types of property is significant for a variety of reasons. Firstly, classification ensures the proper application of the law. This is because the legal regime that governs goods depends on their nature and accordingly their legal treatment substantially varies. For instance, one's rights on movables are more attenuated than one's rights on immovable (or real property). The statutes of limitations or prescriptive periods are usually shorter for movable than immovable property. Besides, real property rights are usually enforceable for a much longer period of time and, in most jurisdictions, real estate and immovable are registered in government-sanctioned land registers. More essentially, the manner for transfer of the possession or ownership of things depends on their nature. For example, the possession of ordinary corporeal chattels (movable things) may be transferred upon delivery. On the contrary, possession of immovable things requires more additional formalities like registration. In short, classification of property has a paramount importance in facilitating legal regulation of property rights and economic transactions.
A law that has been in force since 2005 (Federal Courts Proclamation 454/2005) declares that interpretations of law rendered by the Cassation Division of the Federal Supreme Court (hereinafter referred to as CDFSC), are binding on all federal and state courts. However, according to the same law, this does not prevent the CDFSC from providing a different interpretation in the future.
በአንጌሳ ኢቲቻ የተጻፈውን ‹‹ችሎት መድፈር፡- ሕጉና የአሠራር ግድፈቶች›› የሚለውን ሳነብ እ.አ.አ በታኅሣስ 2013 በተመሳሳይ ርዕስ የጻፍኩትን ለአንባብያን ለማካፈል ወደድኩ፡፡ በዚህ ጽሑፌ ፍርድ ቤት መድፈር ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ሕግ ስለ ፍርድ ቤት መድፈር ምን ይላል? የሕጉ ዓለማስ ምንድነው፣ የወንጀሉ አወሳሰን ልዩ ባህርይስ እንዴት ይታያል፣ በአፈጻጸም የሚታዩ ችግሮች ምንድናቸው የመሚለውን እዳስሳለሁ፡፡
ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እጅግ መሠረታዊ መብት ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩ ሀገራት ሕጋዊ ጥበቃ የሚያደርጉለት ሲሆን በአለማችን ላይ በአንባገነንነታቸው የሚታወቁ መንግሥታት ሰይቀሩ መብቱ ሳይሸራረፍ በሀገራቸው እንደሚጠበቅ ይከራከራሉ። በዚህ ጽሑፍ ሀሳብን በነፃነት መግለጽ መብት በሰፊው ከሚተገበርበት ስለ መገናኛ ብዙኃን መብት እንመለከታለን። በመጀመሪያው ክፍል የመገናኛ ብዙኃን ለምን የሐሰት ዘገባዎችን ይሠራሉ በተለይም በመንግሥት ይዞታ ሥር የሚገኙ ወይም ዋነኛ የፋይናንስ ምንጫቸው በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ከመንግሥት የሆነ የሚለውን እናያለን። በመቀጠል የመገናኛ ብዙኃን የሰሩት ፕሮግራም እውነታን ያዘለ ሆኖ ሳለ የእርምት ወይም መልስ የመስጠት መብት ያለው አካል ሐሰተኛ ማስተባበያ ይዞ ቢቀርብ የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው ወይስ የለባቸውም የሚለውን እንመለከታለን። በመጨረሻም ነፃ ሚዲያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከሀገራችን ሕጎች አንፃር አጭር ዳሰሳ እናካሔዳለን።
ሀገሬው የዳኝነትን ሥራ (ፍትሕ መስጠት) ሃሳባዊ በማድረግ ደረጃውን ከፍ ሲያደርገው “ዳኛ እግዜር!” ይላል፡፡ ከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላትም ዳኛ ማሪያም! ተሙዋጋች በዳኛ ፊት ቆሞ ሲአመለክት ዳኛ እግዚአብሔር! ያሳይህ ዳኛ ማርያም ወይም ሲሙአገት ጭብጥ የያዘውን አስመስካሪውን ዳኛ የምስክሮቹን ቃል ለማሳሰብ ተዘከረኝ ዳኛ ማሪያም ይላል በማለት ይገልፀዋል፡፡ እንደ ፕልቶ ያሉ ሃሳባውያን (idealist) ፈላስፎች “ፍትሕ” ሃሳባዊ ተፈጥሮ ያለው፣ ከሰብዓዊ ባህርይ ውጪ የሆነ እና አሁን ባለው ዓለም (physical world) ሳይሆን በጊዜ እና በቦታ ባልተገደበው ሃሳባዊ ዓለም የሚገኝ እንደመሆኑ ስሙ ብቻ የሚታየውን ሃሳብ ቅርፅ ወዳለው ድርጊት በሕግ መልክ ሆነ በሌላ ዘዴ ወደ ዚህኛው ዓለም ሊመልሱት እና ሊፈፅሙት የሚችሉት እውነተኛው ሃሳብ የሚታያቸው ሰዎች ናቸው ይላል፡፡ እንግዲህ ሀገሬው “ዳኛ እግዜር” ሲል በፍትሕ ላይ ሃሳባዊ መሆኑ ነው፡፡ “ፍትሕ ከፈጣሪ ነው” ብሎ ለሚያምን ማህበረሰብ ሰው በፈራጅነት ቦታ ቁጭ ብሎ ሲያገኘው በአገረኛ ዘዬ ኧረ! ዳኛ እግዜር! ቢል አይገርምም፡፡ ሌላው ሀገሬው በፍትሕ ላይ ሃሳባዊ ለመሆኑ መገለጫ የሚሆነው ለዳኛ ሲሰጠው የነበረው ልዩ ቦታ ነው፡፡ የአንድ ማህበረሰብ ወግ እና ሥርዓት የሚቀዳው ካለው አካባቢያዊ የእምነት እና አስተሳሰብ መሠረት አድርጎ ነው፡፡ ለማሳያ ያህል ከፍትሐ ነገስቱ አንድ ነገር አንጠልጥለን እንውጣ፡፡
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 አንድ ሰው በተጀመረ ክርክር መብቴ ይነካል፤ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብቼ ልከራከር ብሎ ሲጠይቅ እና በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 418 ለፍርድ ማስፈፀሚያ የተያዘ ወይም የተከበረ ንብረት ይለቀቅልኝ በማለት አቤቱታ ሲያቀርብ የዳኝነት ይከፈላል ወይስ አይከፈልም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ሰዎች ኑሮአቸውን ስኬታማ ለማድረግ በሚፈጽሙት የእለት ተእለት ተግባራቸው ከሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎች ጋር ዘርፈ ብዙ መስተጋብሮችን የሚፈጽሙ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና እነኚህን መስተጋብሮች በተለያዩ ምክኒያቶች በራሳቸው ለመፈጸም የማይችሉ በሆነ ጊዜ ሥራዎችን ሌላ ሰው እንዲያከናውንላቸው ፍላጎት ሊያድርባቸው እንደሚችል የሚያሻማ አይደለም፡፡ በዚሁ መሠረት ይህንኑ ሥራቸውን ማን፣ መቼ፣ በምን ሁኔታ እና በድካም ዋጋ ክፍያ ወይም ያለ ክፍያ ሊሠራላቸው እንደሚገባ የመወሰን ነጻነት ሊኖራቸው የተገባ ነው፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በሰበር ችሎት ዉሳኔዎች ቅጽ 14 መግቢያ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፤ “ለተመሣሣይ ጉዳዮች በጣም የተራራቁ ዉሣኔዎችን በመስጠት ይታይ የነበረዉን ችግር በመቅረፍና የዉሣኔዎችን ተገማችነት በማረጋገጥ ረገድ የሰበር ዉሣኔዎች አስገዳጅ መሆን ከፍተኛ ዉጤት አስገኝቷል ማለት ይቻላል፡፡ አልፎ አልፎ በዉሣኔዎች ጥራትና ስርጭት ሊታዩ የሚችሉ ችግሮች ሥርዓቱ እየተጠናከረ ሲሄድ የሚፈቱ ሲሆን አነዚህን ችግሮች ለማቃለል እኛም ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ጥረታችን ሊሳካ የሚችለዉ በዉሣኔዎቹ ላይ በሕግ ምሁራንና ባለሙያዎች ገንቢ የሆኑ ትችቶችና አስተያየቶች ሲቀርቡ ነዉ”፡፡ እኔም ይህን ግብዣ በመቀበል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ትችቴን ከዚህ በመቀጠል አቀርባለሁ፡፡ ዉሳኔዉ የተሰጠዉ በማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ እና ታዬ አበራ መካከል ባለዉ ክርክር በሰበር መዝገብ ቁጥር 72341 ነዉ፡፡ በዚህ መዝገብ ከተነሱት ዋነኛ ጉዳዮች ዉስጥ፤ አላግባብ የተከፈለ ጡረታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይ፤ ከታገደስ የይርጋ ዘመኑ ምን ያህል ነዉ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ፊልሞችን ሰርቶ ለሕዝብ ማቅረብ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ላይ የተቀመጠው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አንደኛው መገለጫ ነው፡፡ ሀሳብን የመግለፅ መብት ከመንግሥት ገደብ (Limitation) ሊጣልበት የሚችለውም ውስን በሆነ ምክንያት እንደሆነ ይሄ ሕግ መንግሥት የሚያስቀምጠው ጉዳይ ነው (አንቀጽ 29/6ን መመልከት ይቻላል)፡፡ አዋጅ ቁጥር 533/2007 እና ከዛ በፊት የወጡ ሕጎችም ትልቅ ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሊገደብ የሚችልበትን አግባብ ያስቀምጣሉ፡፡ ሀሳብን የመግለፅ መብት በሕግ የሚገደበውም ሦስት መሠረታዊ ፍላጎቶችን (Interests) ለመጠበቅ ሲባል ብቻ ነው፡፡ እነዚህም፡-
በከተማችን ሰማይ ላይ የሰፈረ መንፈስ አለ የሆነ ህጻኑን ወጣቱን አዛውንቱን የሚፈታተን መንፈስ፡፡ በራዲዮ ቢራ፣ በቴሌቭዥን ቢራ፣ በቢልቦርዶች ገፅ ላይ ቢራ ሆኗል ከተማው፡፡ ዛሬ ዛሬ ቢሮ ከሚለው ስም ይልቅ ቢራ የሚለውን ስም መስማት የተለማመደ ሆኗል፡፡ እኔም በእለት ተእለት እንቅስቃሴም ውስጥ በሁለት ነገሮች እርግጠኛ ነኝ ከእሁድ በስተቀር ቢሮ እንደምገባና አንድ የቢራ ማስታወቂያ ጆሮየ እንደሚሰማ፡፡ ከወዳጅ ዘመዶቼ ይልቅ አዲሱ ዓመት መልካም እንዲሆንልኝ አብዝተው የተመኙልኝም የቢራ ማስታወቂያዎች ናቸው፡፡ ቢራ ስትጠጣ አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና የብልፅግና ይሆንልሀል ዓይነት ፉገራ እየፎገሩኝ፡፡ ይህን ያህል ቢራ የሕይወታችን ገፅታ ሆኗል፡፡ ስለቢራ ላለመስማት ብር ብሎ ከመጥፋት ውጭ አማራጭ የለም በመዝናናታችን መኃል፣ በመንገዶቻችን ዳርቻ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቻች ቢራ አለ፤ ቢራ መኖሩ አይደለም ችግሩ፣ ችግሩ ቢራ አብዝቶ መኖሩና እየተነገረበት ያለው መንገድ ነው፡፡ ቢራ የማኅበራዊ የሥነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይታችን ጋሬጣ ሊሆነ በሀገሪቱ ሰማይ ላይ አንዣቧል፡፡