ጸሐፊው በፍትሕ ሚንስቴር የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር ሲሆን በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩንቨርስቲ፣ የሁለተኛ ዲግሪውን በንግድ ሕግ ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት በወንጀል ሕግና ፍትሕ የትምህርት መስክ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ለጸሐፊው ያለዎትን አስተያየት temamosisay@gmail.com ወይም በስልክ ቁጥር 0954872702 ላይ ማጋራት ይችላሉ፡፡

አካለመጠን ባልደረሱ ወጣት የወንጀል ሕግ ተላላፊዎች ላይ የኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ - የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓትና የወንጀል ሕጉን መነሻ በማድረግ

በ1995 የወጣው የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት ለተጠረጠሩና ለተከሰሱ ሰዎች በርካታ የሕግ ጥበቃዎችን ያደርጋል። እነዚህ ጥበቃዎች በዋናነት በሕግ ፊት በእኩል የመታየት፣ በሕግ አግባብ የመዳኘት፣ አላግባብ ቤታቸውና አካላቸው ከመበርበር የመጠበቅ፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ያለመያዝ፣ በጠበቃ የመወከል፣ ንፁህ ሆኖ የመገመት፣ የፍርድ ሂደታቸው በግልፅ ችሎት ፈጣን በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የማድረግ፣ የሚቀርብባቸውን ማስረጃ የመመልከትና መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ፣ ኢሰብአዊ ከሆነና ጭካኔ ከተሞላበት ቅጣት የመጠበቅ እና በአንድ ወንጀል ሁለት ጊዜ ያለመቀጣት መብት ናቸው። እነዚህ መብቶች በአብዛኛው እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ በሆኑ ወይም ለአካለመጠን በደረሱ ወጣቶች ላይ የሚተገበሩ ሲሆን አካለመጠን ባልደረሱ ሰዎች ላይ ሁኔታው የተለየ ሆኖ ይገኛል። በወንጀል ለተጠረጠሩና ለተከሰሱ አዋቂ ሰዎች በሕግ የተቀመጡ ጥበቃዎች አካለመጠን ላልደረሱ ሰዎች ሲከለከሉ ወይም በዝምታ ሲታለፉ ይስተዋላል።

  7394 Hits

ስለ ወንጀል ተጎጂዎች - የአዲስ ዕይታ አስፈላጊነት በረቂቁ የወንጀል ሕግ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ላይ

መግቢያ ፡- ተበዳዮች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ የነበራቸው የተሳትፎ ሚና፡ ጥቅል ምልከታ

በኢትዮጵያ የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና ከነበረበት የማማ ደረጃ በጊዜ ሂደት ‹‹ከማማ የመውረድ›› ያህል ዝቅ እያለ መጥቷል። ሀገሪቱ በዳግም የኢጣሊያ ወረራ ተፈፅሞባት ከመያዝዋ እ.እ.አ ከ 1935 ዓ.ም በፊት በወንጀል ጉዳት ደርሶባቸው በቀጥታ ተበዳይ የሆኑ ሰዎች ወይም የተበዳይ ተወካይና ቤተዘመዶች በደል ካደረሰባቸው ሰው ፍትሕን በገዛ እጃቸው ያገኙ ነበር። ተበዳይ ጥቃት ያደረሰበትን ሰው ሲፈልግ ይበቀላል፣ ሲፈልግ በፍርድ አደባባይ ይከሳል ወይም ለደረሰበት በደል ከተበዳይ ከሳ ይቀበላል። አይ ይህን ሁሉ አልፈልግም ካለም ከሁሉም ታቅቦ ፍትሕን ከእግዚአብሔር እየጠየቀ ይኖራል። በዚህ ጊዜ ምርመራ አጣርቶ ክስ የሚመሰርት የዐቃቤ ሕግ ተቋም በሀገሪቱ አልነበረም። በግለሰቦች መሀከል የሚፈጠር አለመግባባቶችን ‹‹የወንጀል›› ጉዳይ እና የግለሰቦች የፍትሐብሔር ጉዳይ ብሎ የሚከፋፍል የሕግ ስርአት ባለመኖሩ ጥቂት በሀይማኖትና በመንግስት ላይ የሚፈፀሙ በአሁኑ ሰአት የፓለቲካ ወንጀል እየተባሉ ከሚጠሩ ወንጀሎች በስተቀር ሁሉም አለመግባባቶች ላይ ግለሰቦች በራሳቸው ከሳሽ በመሆን ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት ያቀርባሉ ወይም ፍትሕን በእጃቸው ያገኙ ነበር። ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት የሚወስዱ ከሆነ ክስ የመመስረት፣ የተጀመረን ክስ የሟቋረጥ፣ ቅጣትን በመምረጥ ተበዳይ ግለሰብ ሁሉን አድራጊ ነበር። የወንጀል ይዘት ያላቸው ጉዳዮችን ከፍትሀብሔር ጉዳዮች ጋር በማጣመር የጉዳት ካሳን መጠየቅም ይቻል ነበር። በዘመኑ የወንጀል ተበዳዮች በወንጀል ጉዳይ የሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች ነበሩ።

  5079 Hits

በኢትዮጵያ የክስረት ሕግ ነጋዴ ከሰረ የሚባለው መቼ ነው? ከክሥረት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ከወንጀል ሕጉ አንፃር

የንግድ ሥራ ኢትዮጵያውያን ከ 11 ኛው ምዕት አመት በፊት ባህር አቋርጠው ድንበር ሳይገድቧቸው ቤትና ሀገር ያፈራውን ከሌላው ለሙሙላትና ለመቀያየር አሁን የምንጠቀምበት አይነት ገንዘብ ከሌለበት ጊዜ ጀምሮ ንግድን ስራዬ ብለው ሲሰሩት ነበር። ረጅም ጉዞ በሚደረግብት የጥንቱ ንግድ ግን ሁሉ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ያላሰቡት ሽፍታ ከመንገድ ሁሉን ከነጋዴው መዝረፍ፣ የተቀየሩት ንብረቶች ፈላጊ በማጣት ነጋዴውን አትራፊ ከመሆን ይልቅ አክስሮት፣ ለአባዳሪዎች እንግልትና ሲሳይ ይዳርገው ነበር። የከሰረ ነጋዴ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚቆጠረው በስራው የገጠመው ዕድለቢስነት በመሆን ሳይሆን መቅሰፍት የወረደበት ተደርጎ ነው። የከሰረን ነጋዴ በጎሪጥ መመልከት፣ ብድር እንኳ ቢጠይቅ ማንም የማያበድረው በመሆኑ የተነሳ አንዴ ወድቆ የማይነሳ ምሳር የበዛበት የሚሆንበት አጋጣሚ አለ።

  1230 Hits