የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ትኩረት ያልሰጠበት የገበያዉ ሁኔታ እና አተገባበሩ

 

መግቢያ

የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ በሽታዉን ከመቋቋም ጎን ለጎን ኢተዮጵያ ካጋጠማት ችግሮች መካካል አንዱ የገበያ በተለመደዉ የፍላጎትና አቅርቦት መርህ (Demand and supply) አለመሄድ ነዉ፡፡ ይህ ችግር በአብዘኃኛዉ ያደጉ ሃገራት ላይ በተለይ በእንደዚህ አስጊ ሰዓት የመፈጠር እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነዉ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በንጽጽር በአደጉት ሃገራት ያሉ ነጋዴዎች ያዳበሩት የንግድ ስነ ምግባር (Business ethics) ከእኛ የላቀ መሆኑ ነዉ፡፡ በሽታዉን አስመልክቶ በገበያዉ ብዙ አይነት ሸማቹን አደጋ ላይ የጣሉ ነገሮች ከአዋጁም በፊት ይሁን እሱን ተከትሎ እየተከሰቱ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያክል ወደ ጎን /ወደ ታች/ ባሉ ነጋዴዎች የሚደረግ የንግድ ዉድድሩን የሚገቱ ስምምነቶች፤ እነዚህም ስምምነቶች ዋጋን ከፍ ማድረግ፣ መጠንን መቀነስ፣ የንግድ እቃዎችን መደበቅ፣ ሸማቾችን መምረጥ (ማግለል ) እና መሰል ድርጊቶችን ያካተቱ ናቸዉ፡፡ እንዲሁም ነጋዴ ወይንም ነጋዴ ባልሆኑ ሰዎች ደግሞ የማከማቸት ስራዎች በተለይ በከተሞች ላይ ጎልተዉ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸዉ፡፡ ኢትዮጵያ ምንም እንኳን እነዚህን ጉዳዮች የሚገዛ የህግ ማዕቀፍ ማለትም (የገበያ ዉድድር ና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ 813/2006) ቢኖራትም ነገር ግን ችግሩን ለማቃለል ብዙ የአፈጻፀም ጉድለቶች ይስተዋሉበታል፡፡ ይሀንንም አስመልክቶ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ና አሱን የሚያብራራዉ ደንብ ነበር፡፡ ነገር ግን በተጠበቀዉ ደረጃ ሳይሆን ገበያን ከመቆጣጠር አንጻር ትልቅ ክፍተትን ያሳያል፡፡

በዚህ አጠር ያለ ፅሁፍ ላይ አዋጁ ገበያን ከማረጋጋት አንጻጻር ትኩረት ማድረግ የነበረበትን ነገሮች እና ክፍተቶቹን፣ እንዲሁም ደግሞ በአፈጻጸም ደረጃ መሻሻል ያለባቸዉን ነገሮች ለመዳሰስ እንሞክራልን፡፡

 

Continue reading
  5654 Hits