ጦማሪው ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት በ2007 ዓ.ም በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ ሲሆን አሁን በፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤቶች በሕግ አማካሪና በጠበቃነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

ጸሐፊውን mulukenseid29@gmail.com ወይም +251917324914 ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት በተሰጠ የፍርድ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ የአፈጻጸም ክስ በይርጋ ቀሪ ስለሚሆንበት የሕግ አግባብ

መግቢያ

አፈጻጸም ማለት አንድ መብቱ በፍርድ ውሳኔ እንዲከበር ለፍርድ ቤት ክስ ያቀረበ ሰው የፍርድ ውሳኔ አግኝቶ በፍርዱ መሰረት ሳይፈጸምለት ሲቀር ፍርዱ የተፈረደበት ወገን እንደ ፍርዱ እንዲፈጽም የሚገደድበት የሕግ ሥርዐት ነው፡፡ ይህ ስርዐት የሚመራውም በፍትሐብሔር ሥነ- ሥርአት ሕግ ቁጥር 375 ጀምሮ በተደነገጉ ድንጋጌዎች መሰረት ሲሆን በእነዚህ የሕግ ማእቀፎች ተንተርሶ መብቱ እንዲፈጸምልት ሚጠይቅ ወገን የፍርድ ባለመብት ሲባል እንዲፈጽም የሚገደደው ደግሞ የፍርድ ባለእዳ ተብሎ ይጠራል፡፡

Continue reading
  13085 Hits