የንጉሣዊ ሥርዓት መውደቁን ተከትሎ ወደ መንግሥታዊ ሥልጣን የመጣው ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት የመንግሥት ንብረት ለማድረግ በሚል አዋጅ ቁጥር 47/1967 በማወጅ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ይህ አዋጅ ሊታወጅ ያቻለበት ዋነኛ መነሻ ምክንያት “በከተሞች ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቦታዎችና ቤቶች በጥቂት መሳፍንት፣ መኳንንትና በከፍተኛ የመንግሥት ባለ ስልጣኖችና ከበርቴዎች በመያዛቸው እንዲሁም የሀብታም ክፍሎች ያላቸውን ከፍተኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ኃይል ያለ አግባብ በመጠቀም ሰው ሰራሽ የከተማ ቦታ እጥረት በመፍጠር የከተማ ቦታ ዋጋን እንዲወደድ በማድረግ በጠቅላላው የብዝበዛ ሥርዓት ጠንክሮ ለከተማው እድገትና ለብዙኃኑ የከተማ ነዋሪዎች የኑሮ መሻሻል ከፍተኛ እንቅፋት በመሆናቸው” በሚል አዋጁን መሠረት በማድረግ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት የመንግሥት ንብረት ሊሆን ችሏል፡፡
የሟች የውርስ ኃብት ተጣርቶ ከተዘጋ በኋላ የውርስ ኃብት ባለቤትነት ወደ ሟች ወራሾች ይተላለፋል፡፡ በመሆኑም ውርስ ከተዘጋ በኋላ ወራሾች መሀከል ክፍያ እስኪፈጸም ድረስ የሟች ወራሾች በሀብቱ ላይ ያላቸው መብት ምንድነው? ክፍፍሉ ከመፈጸሙ በፊት በጋራ ወራሾች የተያዘ ንብረት በአንደኛው ወራሽ ብቻ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ቢተላለፍ ፈቃዳቸውን ያልሰጡ ወራሾች መብታቸው እስከምን ድረስ ነው? ገዥውን ያለውስ መብት ምንድነው? የውርስ ሀብት ክፍፍል የሚደረግባቸው ስነ-ስርዓቶችንና ክፍፍል ከተደረገ በኋላ የሚገኙ የውርስ ኃብት የሆኑ ንብረቶች ለወራሾች ሊከፋፈሉ የሚችሉባቸው የህግ ስርዓቶችን በተመለከተ በወራሾችና ወራሽ ባልሆኑ ሶስተኛ ወገኖች መሀከል እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የደረሱ አከራካሪ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ነጥቦች በተመለከተ ከፍትሐብሔር ሕጉና ከተመረጡና አስገዳጅ ከሆኑ የሰበር ውሳኔዎች አንጻር አጭር ዳሰሳ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡
በዚህ ጽሁፍ በፍትሐብሔር ሕጉ ስለ ውል በተደነገገው ክፍል ስር የተጠቀሱ አጠቃላይ የይርጋ ድንጋጌዎችንና በልዩ የውል ሕግ ክፍል በተለይም የስጦታ ውል፣ የአደራ ውል፣ የሽያጭ ውል ውልን መሰረት በማድረግ የተደነገጉ የይርጋ ድንጋጌዎችንና የመያዣ ውል ቀሪ ስለሚሆንበት የሕግ አግባብ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ከሆኑ የሰበር ውሳኔዎች አግባብ ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍ የይዞታ ትርጉም ምን እንደሆነ፣ ይዞታን መሰረት ያደረገ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በምን አግባብ ሊቀርብ እንደሚችልና ይህ ክስ ከባለቤትነት ክርክር ጋር ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ፣ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ክስ ሲቀርብ ፍርድ ቤቶች የሚይዙት ጭብጥ በተመለከተ ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ትርጓሜው ምን እንደሆነና ቀዳሚ የመግዛት መብት ካለው መሀከል ባልና ሚስትን፣ ወራሾችን በተመለከተ በህጉ ሊስተናገዱ የሚችሉበት አግባብ ለማየት ተሞክሯል፡፡ በስተመጨረሻም የቅድሚያ ግዥ መብት ያለው ሰው በሚገዛበት ጊዜ ስላለው የሽያጭ ስነ-ስርዓት፣ ግድግዳና ጣራቸው በአንድ በኩል የተያያዙ ቤቶችን በተመለከተ በቅድሚያ ግዥ መብት ሊስተናገዱ የሚችሉበት የህግ አግባብና የዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብትን እስመልክቶ በጽሁፍ በወፍ በረር ቅኝት ተደርጎበታል፡፡
በፌዴራሉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 2 እስከ 4 በተጠቀሱት ድንጋጌዎች ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት፣ በኃይማኖት እና በባሕል ሥርዓት መሠረት ሊፈጸም ይችላል፡፡ ከእነዚህ የጋብቻ መፈጸሚያ ስርዓቶች ውስጥ በአንደኛው ስነ-ስርዓት ጋብቻ የተፈጸመ እንደሆነ በጥንዶቹ መካከል በሕግ እውቅና የተሰጠው የትዳር ግንኙነት ተመስርቷል ይባላል፡፡ ጥንዶቹ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት የጋብቻ መፈጸሚያ መንገዶች ውስጥ በአንዱ ጋብቻ ቢፈጽሙ የጋብቻ ውጤትን መሠረት በማድረግ በሕግ የጋራ እና የግል ንብረቶቻቸው ላይ የሚኖረው ውጤት ተመሳሳይ ነው፡፡
መግቢያ
በዚህ ጽሑፍ የሽያጭ ውል ምንነት፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው ስላለው መብትና ገዥው ስለሚኖርበት ግዴታ፣ የሽያጭ ውልን መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ክርክሮች ይዘታቸው እና የይርጋ ገደባቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው ንብረቱን ሊለቅ የሚችልባቸው የሕግ አግባብ ምን ምን እንደሆኑ ከፍትሐብሔር ሕግ እና ከሰበር ውሳኔዎች አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
መግቢያ
ጋብቻ የተፈጸመበት ስነ-ስርዓት ማናቸውም አይነት ቢሆንም የጋብቻ መፍረስ የሚያስከትለው ውጤት ተመሳሳይ ነው፡፡ ጋብቻ ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ ወይም ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በሕግ ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ሊፈርስ ይችላል፡፡
የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ ኑዛዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሰጠው ትርጉም ባይኖርም አንድ ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር የሚያስቀምጡ የሕግ ድንጋጌዎችን ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 857 እስከ 908 ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ጽሁፍ ኑዛዜ በምን አግባብ ቢደረግ በሕግ ዘንድ ውጤት ይኖረዋል፤በውርስ ሕጋችን ላይ የተቀመጡት የኑዛዜ አደራረግ ስርዓቶች አስገዳጅነታቸው እስከምን ድርስ እንደሆነና ኑዛዜ በፍርድ ቤት ቢጸድቅ ሊያስገኝ የሚችለው ውጤትና ባለመጽደቁ የሚያመጣው ተጽእኖ ምን እንደሆነ ከውርስ ሕግ እና አስገጋጅ ከሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ውሳኔዎች አንጻር በአጭሩ ዳሰሳ ለማድርግ ተሞክሯል፡፡
Introduction
The Federal Court Proclamation no 25/96 its amendment, which has been in force for many years, is repealed and replaced by the federal courts' Proclamation number 1234/2021. When we look at the existing proclamation, the new law introduced new elements. In these short notes, we will briefly explore the new features of the proclamation and the reason behind the improvements of the proclamation to its current content.
Introduction
Before the enactment of movable property security right proclamation, Ethiopian movable security right law is ultimately unsatisfactory because it is fragmented, and contained in four different pieces of legislation: The Civil and Commercial Codes, the Business Mortgage Proclamation, the Proclamation to Provide for a Warehouse Receipts System (Warehouse Receipts Proclamation), and the Capital Goods Leasing Business Proclamation. Under this system, security rights in many movable assets are not registered.