ይህን ለመጻፍ ያስገደዱኝን እና የገጠመኙን ሁኔታዎች በቅድሚያ ላብራራ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ሰራተኛ አሰሪው በነበረው ድርጅት ላይ ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ ተፈጽሞብኛል በማለት ላቀረበው ክስ አሰሪው ድርጅት በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ ሰራተኛው የስራ ውሉን ስላቋረጠ ካሳ እንዲከፍለኝ የሚልና ሰራተኛው ስራ ላይ በነበረ ጊዜ ለስራው አገልግሎት የተሰጠውን ላፕቶፕ ኮምፒውተር ሳይመልስ በመቅረቱ ንብረቱን እንዲመልስ ወይም የንብረቱን ግምት ብር 23,000 (ሃያ ሶስት ሺ) እንዲከፍለኝ በማለት ክስ አቀረበ፡፡ ጉዳዩን ሲያይ የነበረው የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የስራ-ክርክር ችሎትም በድርጅቱ የላፕቶፕ ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ይህ ችሎት (ልብ በሉ ፍ/ቤቱ አይደለም)…