የመንጃ ማህበረሰብ ብሄረሰብ ለመሰኘት የሚያበቃ መመዘኛ አያሟላም - የፌዴሬሽን ም/ቤት

FanaBC Jun 05 2014

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንጃ ማህበረሰብ ብሄረሰብ ለመሰኘት የሚያበቃ መመዘኛ አያሟላም በማለት የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የመንጃ ማህበረሰብ  የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረበውን ይግባኝ ተከትሎ ነው።

የመንጃ ማሀበረሰብ አባለቱ ማንነታችን ልዩ ነው ይህም እውቅና ይሰጠው በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ውድቅ አድርጎታል።

ምክር ቤቱ ይህን ሲወስን ማህበረሰቡ የተለየ ማንነት የለውም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ያለውን መስፈርቶች አያሟላም በማለት እንደሆነ በፌድሬሽን ምክት ቤት የህገ መንግስትና የክልሎች ቋሚ ኮሚቴ ፀሃፊ አቶ ዳንኤል ደምሴ ተናግረዋል።

አቶ ዳንኤል  የፌድሬሽን ምክር ቤት የማህበረሰቡ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሌሎች ውሳኔዎችን አሳልፏል ነው ያሉት።

የኮንቱማና የቅማንት ማህበረሰቦች ያቀረቡትን የብሄረሰብነት ጥያቄም እየመረመረ እንደሚገኝ ነው ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ያስታወቀው።

Read 32921 times