የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለየያ የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፎ አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ከ 250 በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ጀመረ ። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮሚሽኑ የወንጀል ድርጊት የሚፈጸምባቸውን ክፍለ ከተሞች በጥናት ከለየ በኋላ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ።
የመኪና እቃ ስርቆት፣ በቡድን በመሆን ማጅራት መምታትና ሌሎችም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንዲካሄድባቸው ካደረጉ የወንጀል ድርጊቶች መካከል ናቸው ።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተካሄደው የስርቆት ተግባር የተለያዩ ንብረቶች በአሁኑ ጊዜ በኮሚሽኑ ተይዘው እንደሚገኙ ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ለፋና ብሮድካስቲነግ የተናገሩት ። ተጠርጣሪዎቹ ፍርድቤት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁንም ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በቅርቡ በተመሳሳይ ሁኔታ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው 200 ከሚሆኑ ተጠርጣሪዎች መካከል አብዛኛዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው በእስራት ተቀጥተዋል። ምክትል ኮምሽነር ግርማ ካሳ ህዝብን በማሳተፍ ወንጀልን የመከላከሉ ተግባር በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥልም ነው የገለፁት። (Source: አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.))