Latest blog posts

እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብዬ ጉዳዬን የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውና በይግባኝ የአፄ /ስላሴን ፊት ማየት አልፈቅድም፡፡

በእግዚያብሔር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሀዘኔ ይበዛል፡፡ 

እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛ ሕግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር፡፡ በአጭሩ በእኔ ላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል አስር እና አስራ አምሰት ዓመት በቀጠሮ የምታጎላሉትን ሕዝብ ጉዳይ እንደዚህ አፋጥናችሁ ብትመለከቱትና ብትሸኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገም ነበር፡፡

  መንግስቱ ንዋይ

ለኢትዮጵያዝብ አንድነት፣ ነፃነትና ርምጃ የተነሳሁ ወዳጅ ነኝ እንጂ ለማፋጀት የተነሳሁ ወንበዴ አይደለሁም፡፡ ይህንን ማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ ማንም የማይወዳደረው ሰራዊትና መሣሪያ ሳላጣ ዛሬ እዚህ ከእናንተ ፊት ለመቆም ባልበቃሁ ነበር፡፡

እኔ ከኃ/ስላሴ ድንክ ውሾች ያነሰ ደመወዝ የሚያገኙ ሁለት የተራቡ ወታደሮችን አጣልቼ ለማደባደብና አገር ለማፍረስ አለመምጣቴን የሚያረጋግጥልኝ እናንተ በትዕዛዝ ያገኛችሁትን ፍርድ ለመቀበል እዚህ መቆሜ ነው፡፡

ከእኔ በፊት በግፍ የፈሰሰው ንፁህ የኢትዮጵያዊያን ደም ብዙ ነው፡፡ በየአፄ /ስላሴ ዘመነ መንግስት ግፍ ሽልማት በመሆኑ እኔ ለመሞት የመጀመሪያው ሰው አልሆንም፡፡ ሥልጣን አላፊ ነው፡፡ እናንተ ዛሬ ከጨበጣችሁት የበለጠ ስልጣን ነበረኝ፡፡ ሀብትም አላጣሁም፡፡ ነገር ግን ሕዝብ የሚበደልበትልጣንና ድሃ የማይካፈለው ኃብት ስላልፈለግሁ ሁሉንም ንቄ ተነሳሁ፡፡ አሁንም እሞታለሁ፡፡ ሰው ሞትን ይሸሻል፡፡ እኔ ግን በደስታ ወደሞት እሄዳለሁ፡፡

ለኢትዮጵያ ኽዝብ ታላቅነት ቀድመውኝ መስዋዕት የሆኑትን አብረውኝ ተነስተው የነበሩትን ጀግኖች ወንድሞቼን ለመገናኝት ናፍቄአለሁ፡፡ የጀመርኩት ሥራ ቀላል አይደለም፡፡ አልተሸነፍኩም፡፡ ወገኔ የሆነው ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመርኩለትን ሥራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ፈፅሞ ራሱን በራሱ እንደሚጠቅም አልጠራጠርም፡፡

ከሁሉ በበለጠ የሚያስደስተኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልሰራለት ካሰብኳቸው ስራዎች አንዱ የኢትዮጵያ ወታደር ዋጋና ክብር ከፍ ማድረግ ሲሆን ይህ ሃሳቤ ህይወቴ ከማለፉ በፊት ሲፈፀም ማየቴ ነው፡፡

ዛሬ መኖራችሁን በማየቴ ነገ መሞታችሁን ረስታችሁ አሜን ብላችሁ ቀናችሁን በማስተላለፍ በመገደዳችሁ በእኔ ላይ ሳትፈርዱ በራሳችሁ ላይ የፈረዳችሁ መሆናችሁን አላስተዋላችሁም፡፡

እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛ ሕግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር፡፡ በአጭሩ በእኔ ላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል አስር እና አስራ አምሰት ዓመት በቀጠሮ የምታጎላሉትን ሕዝብ ጉዳይ እንደዚህ አፋጥናችሁ ብትመለከቱትና ብትሸኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገም ነበር፡፡

ከእናንተ ከዳኞቹና የሞት ፍርድ እንድትበይኑብኝ ካዘዛችሁ ሰው ይልቅ እኔ ፍርድ ተቀባይ የዛሬ ወንጀለኛ የነገ ባለታሪክ ነኝ፡፡

የኔ ከጓደኞቸ መካከል ለጊዜው በህይወት መቆየትና ለእናንተ ፍርድ መብቃት የመመዘኑን ፍርድ ለመጭው ትውልድ የሚያሳይ ይሆናል፡፡

! ! ! ለእናንተና ለገዢአችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚወርድባችሁ መዓት አሰቃቂ ይሆናል፡፡ በተለይ የአፄ /ስላሴ የግፍ መንግስት ባላደራዎች ሆነው ድሀውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገሸልጡት ከነበሩት መኮንን /ወልድና /ወልድ እንግዳወርቅን ከመሳሰሉት በመንፈስ የታሰሩ በስጋ የኮሰሱ መዠገሮች መካከል ጥቂቶቹን ገለል ማድረጌን ሳስታውስና የተረፉትም ፍፃሜያቸውን በሚበድሉት በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ ላይ መውደቅ ሲሰማኝ ደስ ይለኛል፡፡

መንግስቱ ንዋይ : መጋቢት 19 1953 . 

 

 


Editors Pick

About the Law Blog
A law that that has been in force since 2005 (Federal Courts Proclamation 454/2005) declares that interpretations of law, rendered by the Cassation Division of the Federal Supreme Court (hereinafter r...
10964 hits
Criminal Law Blog
መግቢያ ፡- ተበዳዮች በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ የነበራቸው የተሳትፎ ሚና፡ ጥቅል ምልከታ በኢትዮጵያ የወንጀል ተጎጂዎች በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና ከነበረበት የማማ ደረጃ በጊዜ ሂደት ‹‹ከማማ የመውረድ›› ያህል ዝቅ እያለ መጥቷል። ሀገሪቱ በዳግም የኢጣሊያ ወረራ ተፈፅሞባት ከመያዝዋ እ.እ.አ ከ 19...
194 hits
Opinion/Critiques/Case Comment/Public Lecture
  ይህን ለመጻፍ ያስገደዱኝን እና የገጠመኙን ሁኔታዎች በቅድሚያ ላብራራ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ሰራተኛ አሰሪው በነበረው ድርጅት ላይ ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ ተፈጽሞብኛል በማለት ላቀረበው ክስ አሰሪው ድርጅት በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ ሰራተኛው የስራ ውሉን ስላቋረጠ ካሳ እንዲከፍለኝ የሚ...
13635 hits
Construction Law Blog
መግቢያ ይህ ጹሑፍ በ6ኛው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ “የኮንስትራክሽን ዋስትና ሕጎች እና የገንዘብ ተቋማት አሰራር” በሚል አውደ ጥናት ላይ ለውይይት የቀረበ ነው፡፡ ዋስትና በውል አፈጻጸም ወቅት እንደተጨማሪ ግዴታ የሚቆጠር በሕግ ፊት ሊጸና የሚችል (juridical act) ተግባር ነው፡፡ ...
15610 hits

Top Blog Posts

Labor and Employment Blog
  ዓለማችን ላይ የፈረንጆቹ 2020 የተወሳሰቡ ችግሮችን ይዞባት መጥቷል፡፡ ከቻይና ውሃን በትንሹ ተነስቶ በወራት ውስጥ ዓለምን ካዳረሰው የኮሮና ቫይረስ የሚስተካከል ችግር ግን ይመጣል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡ ይህ ቫይረስ በቀጥታ በሰው ልጆች ጤና እና ህይዎት ላይ እያሰከተለ ከሚገኘው ኪሳራ እና ውድመት በሚስተካከ...
Taxation Blog
  በዚህ ጽሑፍ ስለ ግብር ስወራ ምንነት፣ በተለያዩ የግብር ዓይነቶች ሥር የግብር ስወራ ስለሚያቋቋሙ ድርጊቶች፣ ለግብር ስወራ መነሻ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምክንያቶች እንዲሁም የመከላከያ መንገዶቹ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉምሩክና ታክስ ወንጀል ችሎት...
About the Law Blog
  መግቢያ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀደም ሲል አውጥቶት የነበረውና የተከራየን ሰው ማስወጣት (በርግጥ ደንቡ ይህን ድርጊት አልከለከለም) እና የኪራይ ዋጋን መጨመር ለማገድ የወጣውን የደንብ ቁጥር 122/13 ማራዘሙን በድጋሜ አስታዉቋል፡፡ ይህ ደንብ የቤት አከራዮች ያከራዬት ቤት ላይ ዋጋ እንዳንይጨምሩ ...
Taxation Blog
It is perplexing for me, as a tax lawyer having worked for close to 10 years on Ethiopian tax laws, to see how the investment and finance community in Ethiopia is not worrying enough about the tax on ...