የታክስ አስተዳደር ቅጣት አነሳስ መመሪያ ቁ____/2016

የገቢዎች ሚኒስቴር በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 115(4) በተሰጠው ሥልጣን የታክስ አሰተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ ሲሆን በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያያት ያለው ስው አስተያየቱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣውበት ግንቦት 08/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ለገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማቅረብ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

መመሪያ ቁጥር 159/2016 በመንደር የንግድ ቁጥጥር የአሠራር ሥርዓት

1325/2024

ምክር ቤቱ የሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ

(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 6፣ 2016 ዓ.ም.፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው የሜዳይ፣ ኒሻንና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክተው እንደገለጹት በአገራችን፣ በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅም የላቀ ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና አካላትን እውቅና በመስጠት ትውልዱን ማነሳሳት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በህገ-መንግስቱ መሰረት ማስፈጸሚያ አዋጅ ሳይወጣላቸው እየተሰጡ ያሉ የተለያዩ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ሂደቶችን በማስቀረት ወጥ የሆነ ህጋዊ አሰራር እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ መሆኑንም የተከበሩ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) አክለዋል፡፡

ምክር ቤቱም የተሰጠውን ማብራሪያ ተቀብሎ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1325/2016 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

የመጨረሻው ረቂቁ ከስር ተያይዟል

👇👇👇👇

አዋጅ ቁጥር 1324/2016 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1324/2024